ጅማ አባ ጅፋር እና መከላከያ የቻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬና ነገ ያከናውናሉ
ጅማ አባ ጅፋር እና መከላከያ የቻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬና ነገ ያከናውናሉ
አርትስ ስፖርት 25/03/2011
በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ እየተካፈለ የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋር በቅድመ ማጣሪያው ከጅቡቲው አሳስ/ጅቡቲ ቴሌኮም ጋር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም 10፡00 ላይ ያከናውናል፡፡ በመጀመሪያው ጨዋታ የጅማው ቡድን ከሜዳው ውጭ የ3 ለ 1 ድል ውጤት ይዞ መመለሱ ይታወሳል፡፡
ጅቡቲ ቴሌኮም 27 የልዑክ ቡድን አባላትን በመያዝ አዲስ አበባ ገብቷል፤ አባ ጅፋር በአጠቃላይ ውጤት ወደ ተከታዩ ዙር የሚሻገር ከሆነ የግብፁን አል-አህሊን የሚገጥም ይሆናል።
የመልስ ጨዋታውን ደግሞ ኬንያውያን ዳኞች ይመሩታል፤ ፒተር ዋዌሩ የመሀል አርቢትር ናቸው፡፡
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ደግሞ መከላከያ ባለፈው ሳምንት ኢኑጉ ላይ ከናይጀሪያው ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል ጋር ተጫውቶ የ2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዶ መመለሱ ይታወሳል፤ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡
በአሰልጣኝ ስዩም አባተ የሚመራው የጦሩ ቡድን ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ ለመሻገር ከሁለት ግቦች በዘለለ ድል ማድረግ ይጠበቅበታ፡፡ የመልስ ግጥሚያውን ሩዋንዳውያን ዳኞች ሲመሩት ሳሙኤል ኡዊኩንዳ የመሀል ዳኛ ናቸው፡፡