loading
ጋሕአዴን ሶስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን እስከቀጣይ ጉባዔ ድረስ አገደ

ጋሕአዴን ሶስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን እስከቀጣይ ጉባዔ ድረስ አገደ

አርትስ 20/02/2011

 

የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ላለፉት ዘጠኝ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ጉባዔ ማጠናቀቁን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫዉም ጋሕአዴን የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ የክልሉን ሕዝቦች ፍላጎት ለማርካት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ ነው ብሏል።

ድርጅቱ በቅርቡ በክልላችን ላጋጠመው የፀጥታ ችግር ዋና ምክንያት ከፍተኛ አመራሩ ለስልጣን ካለው የተበላሸ አተያይ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ለ10 ቀናት ካደረገው ግምገማ በመነሳት የድርጅቱን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ለችግሩ ራሳቸው ግንባር ቀደም ተጠያቂ በማድረግና ለሌሎች አርዓያ ለመሆን ከሃላፊነታቸውተነስተው በማዕከላዊ ኮሜቴነት ለመቀጠል ያቀረቡትን ጥያቄ ማዕከላዊ ኮሚቴው በሙሉ ድምፅ ተቀብሎታል። በምትካቸውም አቶ ኡሙድ ኡጁሉን ሊቀመንበርና አቶ ተንኩዌይ ጆክን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ በነፃና ዴሞክራሲያዊ ትግል መርጧል።

ከዚህም ሌላ ሶስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን እስከሚቀጥለው ጉባዔ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሲያግድ አንድ የስራ አስፈፃሚ አባልን ደግሞ ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዲወርድ ወስኗል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *