loading
ጓርዲዮላና ሲቲ አሁንም በድል ጎዳና ላይ እየገሰገሱ ነው

ጓርዲዮላና ሲቲ አሁንም በድል ጎዳና ላይ እየገሰገሱ ነው
የእንግሊዝ ኢምሬት ኤፍ ኤ ካፕ የአራተኛ ዙር ጨዋታዎች በርካታ ግጥሚያዎች ትናንት ምሽት ተከናውነዋል፡፡
በዚህም ኢቲሃድ ላይ በርንሊን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ በ5 ለ 0 ሰፊ የግብ ልዩነት ውጤት ድል በማድረግ ወደ ቀጣዩቀጣዩን 5ኛ ዙር ተቀላቅሏል፡፡ ጋብሪዬል ጄሱስ፣ በርናርዶ ሲልቫ፣ ኬቨን ዴ ብሯይኔ፣ የበርንሊው ሎንግ በራሱ ግብ ላይ እና ሰርጂዮ አጉዌሮ በፍፁም ቅጣት ያስቆጠሯቸው ጎሎች ዘ ሲቲዝንስን በአራቱም ውድድሮች በተሰካ ሁኔታ እንዲጓዙ አስችለዋል፡፡ ሲቲ በሊጉ ከሊለቨርፑል ጋር እየተፎካከረ ነው፤ በቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 16ቱ ውስጥ ይገኛል፤ በካራባዎ ዋንጫ ከቼልሲ ጋር በፍፃሜ ይገናኛል፤ አሁን ደግሞ በኤፍ ኤ ዋንጫ ጥሩ ጉዞ ላይ ነው፡፡
ትናንት በተካሄዱ ሌሎች ግጥሚያዎች ዋትፎርድ ኒውካስትልን 2 ለ 0፤ ሚልወል ኢቨርተንን 3 ለ 2፣ ዊምብልደን ዌስትሃምን 4 ለ 2፣ ስዋንሲ ጊሊንግሃምን 4 ለ 1፣ ደርቢ ካውንቲ አክሪንግተንን 1 ለ 0፣ ዶንካስተር ሮቨርስ ኦልድሃምን 2 ለ 1 በመርታት ቀጣዩን ዙር ተዋህደዋል፡፡
ብራይተን ከዌስት ብሮም፣ ሚድልስ ብራ ከኒውፖርት እና ፖርትስማውዝ ከኪው.ፒ.አር በተመሳሳይ 1 ለ 1 አቻ እንዲሁም ሽሮውበሪ ከወልቭስ 2 ለ 2 አቻ በመላያየታቸው የመልስ ግጥሚያ ያከናውናሉ፡፡
ዛሬ ምሽት 1፡00 ላይ ክሪስታል ፓላስ በሴልህረስት ፓርክ ከ ቶተንሃም ሲጫወቱ፤ 3፡00 ላይ ደግሞ ቼልሲ በስታንፎርድ ብሪጅ ሸፊልድ ዌንስዳይን ያስተናግዳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *