ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የወንጀለኞችን ማንንት ሳንመለከት በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ አድነን ለሕግ ማቅረባችን ግን አይቀሬ ነው አሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የወንጀለኞችን ማንንት ሳንመለከት በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ አድነን ለሕግ ማቅረባችን ግን አይቀሬ ነው አሉ
አርትስ 04/04/2011
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ መልዕክት ዙሪያም ትላንት ማምሻዉን መልእክት አስተላፈዋል፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊረጋገጡ የሚችሉት አገር በግለሰቦች ፍላጎት መመራቷ ቀርቶ የጋራ ፍላጎታችን በወለዳቸው ተቋማት መመራት ስትጀምር ነው ብለዋል፡፡
በመንግስት ባለስልጣናት ፈቃጅነትና መሪነት፣ ህሊናቸውን ሸጠው ለሆዳቸው ባደሩ የግፍ ሰራዊት ተላላኪነት፤ በዜጎች ላይ አራዊት የማይፈፅሙት ሰቆቃ ይወርድባቸው ነበር በማለት ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግፍ ፈፃሚዎቹ ከሳሽም፣ ምስክርም፣ መርማሪም፣ አሳሪም፣ አቃቤ ሕግም፣ ዳኛም ሆነው የግፉን ድራማ ተውነውታል፤ እነዚህ ሰዎች ማህበረሰብንም ብቻ ሳይሆን ሰውነትንም አይወክሉም ብለዋል፡፡
እነዚህ ሰዎች ስግብግብነት፣ አምባገነንነትና የስልጣን ጥማት ጫፍ ላይ ሲደርሱ ሰውን እንዴት ወደ አውሬነት እንደሚቀይሩት ማሳያ ናቸውና የግፋቸውን ዋጋ በሕግ እንዲቀበሉ ማድረግ፤ ይህ ግፍ ዳግም እንዳይፈፀም አስተማማኝ ስርዓት መዘርጋት፤ ከእነርሱ የተሻልን መሆናችንን በተግባር ማሳየት አለብን ሲሉ በመልዕክታቸው አስፍረዋል፡፡
ይህ የእነርሱ አረመኔያዊነት ፈፅሞ መደገም የለበትም፤ ይህንን ግፍ የፈጠሩትን ቀዳዳዎች መድፈን፣ ሕጎችን ማሻሻል፣ አሰራሮችን
ማስተካከል፣ ተቋማትን ማብቃት፣ የዝርፊያና የአምባገነንነት በሮችን መዝጋት አለብንም ብለዋል፡፡
በምንም መልኩ ግፈኞቹ ራሳቸውን እንጂ ግፈኞቹ የበቀሉበትን ህዝብ ግፋቸው እንደማይመለከተው እናምናለን፤ የትኛውም ብሔር ወይም የትኛውም ዘር ግፈኞችን፣ ገራፊዎችንና ጨቋኞችን ሊያበቅሉ ይችላሉ፡፡ ወንጀለኞች ማንም ይሁኑ ማን፣ ከየትኛውም ብሔር ገብተው ይደበቁ፣ የትኛውም ወገን ይጩህላቸው፣ በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ አድነን ለሕግ ማቅረባችን ግን አይቀሬ ነው፡፡
አገራዊ ወሰንም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ድንበር ወንጀለኞችን ለፍርድ ከመቅረብ አይታደጋቸውም፡፡ ለዚህ መንግስት ክንዱ ፈርጣማ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡