loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሀገራዊና ቀጠናዊ ዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሀገራዊና ቀጠናዊ ዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያና ጣሊያን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡


ዲ ማዮ አዲስ አበባ ሲገቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በሁለት ቀን ቆይታቸው ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተለያ ጉዳዮች ውይይት የሚያደርጉት የወጭ ጉዳይ ሚስትሩ በሀገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር መክረዋል ነው የተባለው፡፡


ሁለቱ ሀገራት በባህል ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማሻሻል እና በቀጣይም በአዳዲስ ዘርፎች በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ጣልያን ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር አላማ ያደረገ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *