ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

አርትስ 04/04/2011

ውይይቱም በዋናነት የኮሚቴውን የ5 ወራት የግጭት አፈታት እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶችን ገምግሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን የተመዘገበውን ለውጥ በተለይም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የጋራ የሆነ አንድነትን የሚያጠናክር ተቋም መመስረቱን መንግስታቸው እንደሚያደንቅ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታዩትን መግባባቶች ለማጠናከርና እነሱንም ለማደናቀፍ የሚሰሩ ማናቸውንም እንቅፋቶች ለመከላከል መንግስታቸው  ድጋፍ  እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *