loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ዳዊት ዮሃንስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ዳዊት ዮሃንስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአቶ ዳዊት ዮሃንስ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል ይላል ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የወጣው መረጃ።

በተመሳሳይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአዴፓ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንንም በቀድሞ አፈ ጉባኤ ዳዊት ዮሃንስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤትም በመግለጫው በአቶ ዳዊት ዮሃንስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ፅህፈት ቤቱ “የቀድሞው ብአዴን (የአሁኑ አዴፓ) የስራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እንዲሁም የሀገሪቱ የከፍተኛ ስልጣን ባለቤት የሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን የመጀመሪያ አፈጉባኤ በመሆን በማገልገል የኢትዮጵያ ህዝብ እና ድርጅታቸው የጣለባቸውን ሀላፊነት በአግባቡ በተወጡት በአቶ ዳዊት ዮሐንስ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በመላው የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም በኢህአዴግ ምክር ቤት ሰራተኞች ስም እገልጻለሁ ብሏል።

በስራቸው የተመሰገኑ ጠንካራ ታጋይ ነበሩ ያለው መግለጫው፥ በህልፈታቸው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ አጋሮቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ተመኝቷል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *