loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የመከላከያ ሰራዊት በአንዲት ሀገር የሚኖር ብቸኛው የታጠቀ አካል ነው አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የመከላከያ ሰራዊት በአንዲት ሀገር የሚኖር ብቸኛው የታጠቀ አካል ነው አሉ

አርትስ 29/02/2011

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከክፍለ ጦር አዛዦች በላይ ካሉ ወታደራዊ አመራሮች ጋር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባደረጉት ውይይት ላይ ነው፡፡

የመከላከያ ሰራዊት በአንዲት ሀገር የሚኖር ብቸኛው የታጠቀ አካል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያ ሰራዊትን ለማዘመን እና  ብቁ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ  እንደሚቀጥልም ገልፀዋል፡፡

በቅርቡ በውስን ወታደሮች የተከሰተው ከወታደራዊ ስነስርዓት ውጭ የሆነው ድርጊትም እንደ መነሻ መወሰዱን ገልፀው የውይይቱ አብይ አላማ የመከላከያ አመራር ብቁነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአመራር ብቃቶችን እና  የግዳጅ አፈፃፀም ሂደት ላይ ሃይልና ስልጣንን በተገቢው መንገድ በመጠቀም ተቀባይነትን ማግኘት ስለሚቻልባቸው ሂደቶች ነው፡፡

እንዲህ ያሉ ጥሰቶች እንዳይከሰቱ የግዳጅ አፈፃፀም መመሪያዎች እንደሚከለሱና በመመሪያው መሰረት ጥብቅ የእዝና የቁጥጥር ስርዓት በማስፈን  እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት መቋቋሚያ አዋጅ የባህር ሀይል አደረጃጀትን አካቶ እንዲሁም ወደፊት የሳይበርና የህዋ/ስፔስ/ ምህዳሮችን ለማካተት እንዲያስችል ተደርጎ መሻሻሉን እና  ዘመናዊው ዓውደ ውጊያ በሚጠይቃቸው አምስቱም ምህዳሮች ማለትም የምድር፣ ዓየር፣ ባህር፣ ሳይበርና ህዋ ዝግጁ የሆነ መከላከያ ሰራዊት የመገንባት ሂደት መጀመሩ አስታውቀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *