loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚገኙበት የኦህዴድ ጉባዔ የመክፈቻ ሥነ-ስርአት ለነገ ተሸጋገረ

አርትስ 08/01/2011
“የላቀ ሀሳብ ለበለጠ ድል” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ጀምሮ በጅማ እንደሚካሄድ የተገለፀው ድርጅታዊ ጉባዔው የፓርቲዉ ያለፉት ሶስት ዓመታት የድርጅት እና የፖለቲካ ስራዎች የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚሽን ሪፖርት፣ የፓርቲዉ ቀጣይ ስትራቴጂክ አቅጣጫዎች ቀርበዉ ዉይይት እንደሚደረጉበት ይጠበቃል። ፓርቲዉ በዚህ ጉባዔ በአዲስ ስያሜ፣አርማ እና መዝሙር ራሱን ሪብራንድ የማድረግ አጀንዳዎች ላይ ትናንት የጀመረው ውይይት በመቀጠሉ ለዛሬ ታስቦ የነበረው የጉባዔዉ የመክፈቻ ስነስርዓት የድርጅቱ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ በተገኙበት ነገ እንደሚካሄድ ታውቋል። ከ6 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት በደማቅ ስነ ስርአት ይከፈታል ተብሏል ። ከመክፈቻ ስነስርዓቱ በፊት የተጀመረው ውይይት ዛሬም ቀጥሎ ይውላል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *