loading
ፈረንሳይ 10 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለአፍሪካ ልትሰጥ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 የፈረንሳይ መንግስት በሰጠው መግለጫ ክትባቱ በአፍሪካ ህብረት የክትባት ማግኛ ትረስት በኩል ለህብረቱ አባል ሀገራት ይከፋልል ብሏል፡፡ እስከ መጭው መስከረም ወር 2022 ድረስ 400 ሚሊዮን አፍሪካዊያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ የክትባት መጠን ግዥ መፈጸሙን የፕሬዚደንት ማክሮን ጽህፈት ቤት ይፋ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡

ባለፈው ሳምንት በርሊን ላይ በተካሄደ ኮንፈረንስ የአፍሪካ መሪዎች ለአህጉሩ በቂ የክትባት መጠን እንዲሰጥ ጥሪ ማቀውረባቸውን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ በበኩላቸው የበለጸጉት ሀገራት ከጎልማሳ ዕድሜ በላይ ያሉ ዜጎቻቸውን በሙሉ በሚባል ደረጃ እንዲከተቡ ሲያደርጉ እንደ አፍሪካ ያሉ ድሃ ሀገራት ዜጎቻቸው ከ2 በመቶ ያልዘለለ ክትባት ማግኘታቸው ኢፍትሃዊ ነው ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት አህጉሩ በክትባት ራሱን እንዲችል በአምስት ቀጠናዎች የክትባት ማምረቻዎችን ለመገንባት እቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡ እስካሁን ግብፅና ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ክትባትን በራሳቸው አቅም በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመራቸውን ይፋ አድገዋል፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ግን ከአደጉት ሀገራት ጋር ባላቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ከማግኘት የዘለለ አቅም እንደሌላቸው ነው የሚነገረው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *