loading
ፒዮንግያንግ ዋሽንግተን ሃቧን ካልቀየረች ሌላ ምርጫ ውስጥ ለመግባት እገደዳለሁ አለች

ፒዮንግያንግ ዋሽንግተን ሃቧን ካልቀየረች ሌላ ምርጫ ውስጥ ለመግባት እገደዳለሁ አለች

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን አሜሪካ በሀገራቸን ላይ የጣለችውን ኢኮኖሚያዊ ማእቀብ የማታነሳ ከሆነ እኛም የራሳችንን መንገድ እንከተላለን ብለዋል፡፡

የፖለቲካ ታዛቢዎች ግን የኪምን ማስጠንቀቂያ የመደራደሪያ መንገዱን ለመቀየር የዘገየ ነው ብለውታል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ኪም ጆንግ ኡን ሰሞኑን ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመወያት እና የኒውክሌር ጣቢያዎቻቸዉን ከቅድመ ሁኔታ ጋር ለመዝጋት ፍላጎት  እንዳላቸው ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ሊከተሉት ስላሰቡት አዲስ መንገድ ማብራሪያ  ባይሰጡም ሁለቱ ሀገራት ባለፉት ዓመታት የገቡበትን የኒውክሌር ጉዳይ ለማእቀቡ ማንሻ በመያዣነት ለመቅረብ አስበው ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡

አንዳንዶቹ ደግሞ ሰሜን ኮሪያ ከቻይና እና ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት በማጠናከር ዋሽንግተን ላይ ጫና ለማሳደር አስባ ይሆናል ይላሉ፡፡

ለዚህ አንዱ ማሳያ ሰሜን ኮሪያ ከጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ጋር በቅርቡ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ዝግጅት ላይ መሆኗን ይፋ ማድረጓ ነው፡፡

ይሄም ለአሜሪካ እኛ የገባነው ቃል ኒውክሌር ማባላያዎቻቸንን በማወድም አክብረናል፡፡ እናንተ ግን  የጣለችሁብንን ማእቀብ አላነሳችሁም፤ እናም ይሄን ካላደረጋችሁ ሌላ መንገድ እንዳለ ማሳየትም እንችላለን የሚል መልእክት አለው ነው የተባለው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *