loading
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ የተከሰተውን ቃጠሎ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር አይገናኝም አሉ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2013 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ የተከሰተውን ቃጠሎ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር አይገናኝም አሉ::
በካፎርኒያ፣ኦሬጎን እና ዋሽንግተን የተከሰተው ሰደድ እሳት ያደረሰውን ውድመት የጎበኙት ትራምፕ የደን አጠባበቅ ችግር እንጂ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ተርራምፕ በጉብኛታቸው ወቅት ከአካባቢው ባለ ስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይት ጉዳዩን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚያያዙትን አካላት ሀሳብ አጣጥለዋል፡፡

ሳይንሳዊ ትንበያዎችና ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን እንዴት ቸል ማለት ይቻላል ብለው አስተያየት ለሰጡ ሰዎችም ሳይንስ ሁሉንም ነገር ያውቃል ብላችሁ አታስቡ የሚል መልስ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡ ዴሞክራት ፓርቲን ወክለው በምርጫ የሚፎካከሯቸው ጆ ባይደን በበኩላቸው ትራምፕን ለአየር ንብረት ለውጥ ግድ የሌላቸው ባቻ ሳይሆን ሁኔታው እንዲባባስ ተግተው የሚሰሩ በማለት ወቅሰዋቸዋል፡፡

ትራምፕ ሌሎች ሀገራት በደን አጠባበቅ ስርዓት ከኛ የተሸሉ በመሆናቸው የኛን ያህል አደጋ አላስተናገዱም በማለት የባለ ስላጣናቱን ቸልተኝነት ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ከአሁን ቀደም ስለ አየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጠይቀው ጉዳዩ ከአፈ ታሪክነት የዘለለ እውነትነት የለውም ያሉት ፕሬዚዳንቱ የፓሪሱን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ጠቃሚ አይደለም በማለት ጥለው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *