114 ደጋፊ የሌላቸው አዛውንቶች ቤት እድሳት ተጀመረ፡፡
የአዲስ ተስፋ ቀመር ጥላቻን መቀነስ ፤ ያለንን ማካፈል፤ ይቅርታን ማባዛት ፤በፍቅር መደመር ! በሚል አለማ ፤
በአዲስ አመት ደጋፊ የሌላቸውን አዛውንቶች በበጎ ፍቃደኞች ርብርብ ቤታቸውን የማደስ እቅድ ተይዞ በከተማ ደረጃ ካሉ ወረዳዎች እጅጉን የከፉ 114 ቤቶች ተለይተው ወደ ስራ ተገብቷል።
በዚህም መሰረት በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 06 የሚኖሩ አዛውንት ወይዘሮ አበበች ገብረመድህን ቤት ከተለዩት ቤቶች መካከል ይጠቀሳል።
የወ/ሮ አበበችና ሌሎች እንደ እርሳቸው ያሉ ጧሪ የሌላቸው አረጋዊያን ቤቶቹ በእውቅ አትሌቶች ፣ አርቲስቶች ፣ አመራሮች እና በከተማው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተሳትፎና ርብርብ እንደሚታደሱ ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ድረ ገጽ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክተል፡፡