loading
156 ትልልቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ::

ከ4 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ 156 ትልልቅ ኩባንያዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፥ እየተጠናቀቀ ያለው አመት ከኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አኳያ የላቀ ውጤት የተመዘገበበት ነበር ብለዋል።
ቃል አቀባዩ በዋናው መስሪያ ቤት፣ በኤምባሲዎች እና በቆንጽላ ፅህፈት ቤቶች በተሰሩ ስራዎች የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በስፋት እንዲገነዘቡ የማድረግ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
በዚህም ከ4 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ ከ156 በላይ ትልልቅ ኩባንያዎች መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
ቃል አቀባዩ አሁን ላይ ያለው የሰላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣት፣ ሌሎች ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ያላቸው ፍላጎት መጠናከር እና ዳያስፖራዎች በሀገራቸው ጉዳይ የተሻለ ተሳትፎ ለማድረግ በመወሰናቸው በቀጣዩ ዓመት የተሻለ ስኬት እንዲመዘገብ ከወዲሁ ስራ ተጀምሯልም ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *