loading
በሚቀጥሉት ሳምንታት በትንሽ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) መድሃኒት የማድረስ ስራ ይጀመራል፡፡

መድሃኒት የማድረስ ስራው ሳይንስ እና ቴክኖሎጄ ሚኒስቴር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንደሚሰሩት የሳይንስና ቴክኖሎጄ ሚኒስቴር በድረ ገፁ ላይ አስፍሯል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ አመት በትምህርት፤ በጤና በግብርናና በሌሎች ዘርፎች የተሻለ ስራን ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ለመስራት በሚያስችለው ሁኔታ ላይ ከሰራተኞቹ ጋር መክሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ ጎበኙ፡፡

ከጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ በተጨማሪ ዱከም ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጨምሮ በጅማና በቦንጋ የሚገኙ የጫካ ቡናዎችን ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ከመጡ ባለሀብቶች ጋር መጎብኘታቸውን የጅማ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በጉብኝቱ ወቅትም ባለሀብቶቹ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በ61 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር […]

የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች በሀገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች እና እየተባባሰ የመጣውን ስርዓት አልበኝነትን አጥብቀን እናወግዛለን አሉ፡፡

የሀይማኖት አባቶቹ ይህንን ያሉት የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነዉ፡፡ የሃይማኖት አባቶቹ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅጅጋ ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሰው ህይወት መጥፋቱ እና አብያተ ክርስቲያናት መቃጠል የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ነዉ ብለዋል፡፡ በተያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው ስርዓት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት የሃማኖት አባቶቹ […]

ኢትዮጵያ ከቱሪስቶች 3. 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር አገኝች፡፡

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት በ2010 ዓ.ም ኢትዮጵያን ከጎበኙ 934 ሺ ቱሪስቶች 3.5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ ከጎብኝዎች መካከል የቻይና ቱሪስቶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ሲሆን፤ የእንግሊዝ እና የአሜሪካን ዜግነት ያላቸዉ ቱሪስቶችም በብዛት ሀገራችንን ጎብኝተዋል፡፡ ለገቢዉ መገኘት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከባለድርሻ አካላትጋር ዘርፉን ለማሳደግ በጋራ መስራቱና የኢትዮጵያ […]

የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘቱን መቀየሩ አሳስቦኛል አለ::

ይህንን ያለዉ የአዲስ አበባ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ነዉ፡፡ በባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የጋራ ባህል እሴትዳይሬክተር አቶ አለማየው ጌታቸው የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘት እየተቀየረ መምጣቱንና ስነቃሎቹም ላይ ጥናት ሊደረግ መሆኑን ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ባህል እና ቱሪዝም ቡሄን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማደረጉን ገልፀው በመጪው ቡሄ ስነቃላዊ ጥናቶችን ለማድርግ በፌደራል ደረጃ መስሪያ ቤቱ […]