loading
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀጅ ተጓዦች ላይ የተፈጠረውን የበረራ መስተጓጎል ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ የሀጅ ተጓዦች በረራቸው ተሰርዞ በአየር መንገድ ውስጥ ያለ በቂ ምግብና ማረፊያ እየተጉላላን ነው ብለዋል፡ ይህን ተከትሎ አቢሲ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ስልክ ደውሎ ስለ ሁኔታው ለማጣራት ቢሞክርም አየር መንገድ ስለ ጉዳዩ በፌስ ቡክ ገፁ ካወጣው መረጃ ተጨማሪ የሚሰጠው መረጃ እንደሌለው የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል፡፡ አየር መንገዱ በፌስ ቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ በሀጅ […]

ስምንት ኮንቴይነር የታሸገ የኤሌክትሪክ እቃና አልባሳት በህገ-ወጥ መንገድ ሲገባ ተያዘ፡፡

በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ጥሬ እቃ ስም በስምንት ኮንቴነር የታሸገ ያለቀለት የኤሌክትሮኒክስ እቃና አልባሳት ወደ ሃገር ውስጥ ሊገባ ሲል መያዙን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጠቅሶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በድረ ገጹ አስታዉቋል ። በባለስልጣኑ የሞጆ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የጉምሩክ ስነ-ስርዓት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ግርማ በንቲ እንደገለጹት እቃው የተያዘው ተመሳስሎ ሊያልፍ ሲል በሞጆ ደረቅ ወደብ […]

ከእንግሊዝ ፓርላማ የመከላከያ አጥር ጋር የተጋጨ ተሽከርካሪ በርካቶች ላይ አደጋ አድርሷል፡፡

የለንደን ከተማ ፖሊስ እንደዳረጋገጠው በእግረኛ መንገድ ላይ ይጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ ን አደጋው የደረሰው፡፡ እሰውካሁን ቁስለኞቹ ለህይዎታቸው አስጊ ሁኔታ እንዳልደረሰባቸውም የፖሊስ ሃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ያዋለው ሲሆን ገሩን በማጣራት ላይ ነኝ ማለቱን ቢቢሲ፣ ሲ ኤን ኤንና ሌሎች ሚዲያዎችም ዘግበውታል፡፡

የእስራኤሉ የመከላከያ ሚንስትር የጋዛ ጦርነት አይቀሬ ነው አሉ፡፡

የመከላከያ ሚንስሩ አቪገግዶር ሌምበርማን ዘ ጀሩሳሌም ፖስት ለተባለው ጋዜጣ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ጦርነቱ መቸ ነው እንጂ የት ይካሄዳል ብላችሁ አትጠይቁ ብለዋል፡፡ በጋዛ ሰርጥ አስፈላጊውን የጥቃት ርምጃ ለመውሰድ የሚቀረው የጊዜ ጉዳይ ነው ያሉት ሌምበርማን እኛ እስራኤላዊያን ጠንካራና ሀላፊነት የተሞላበት የደህንነት ፖሊሲ እናራምደዳለን ብለዋል፡፡ ይሄን ፖሊሲ ደግሞ ለማህበራዊ ሚዲያና ለጋዜጦች የፊት ጋጽ ማጣበቢያነት ማዋል ሳይሆን መቸና እንዴት […]

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ጥሪ አቀረቡለት

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ወደሀገሩ እንዲመለስ መጋበዛቸውን ያስታወቁት። በመግለጫቸውም በሪዮ ኦሎምፒክ እና በልዩ ልዩ የዓለም አትሌቲክስ መድረኮች በመሳተፍ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አስተዋጽኦ ያበረከተው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ፍላጎታቸው መሆኑን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጁት […]

ከ12 ከተሞች ተገልጋዮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሚሰጠው አገልግሎት አልረካንም አሉ፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ከዋልታ ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር በከተሞች የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ከተሞች የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ቅንጅታዊ አሰራር ሊከተሉ ይገባል ተብሏል፡፡ ከተሞቻችን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር እጦት የሰፈነባቸው የምሬት ማዕከል ሆነዋል ያሉት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስትር አቶ ጃንጥራር አባይ፤ በአመራሮችና ፈጻሚዎች ድክመት፣ የብቃት ችግር ፣ቀልጣፋና ፍትሃዊ […]

ቅዱስ ጊዮርጊስ ጌታነህ ከበደን አስፈረመ፡፡

የቀድሞ የደቡብ ፖሊስ እና የደደቢት እንዲሁም በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቱ የደቡብ አፍሪካዎቹን ቢድቬስት ዊትስ እና ፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ ያሳለፈው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ጌታነህ ከበደ (ሰበሮ) በዛሬው ዕለት ለ2 ዓመት ፈረሰኞቹን ተቀላቅሏል። ጌታነህ ደደቢት ቡድኑን በአዲስ መልክ ለማደረጀት፤ በአነስተኛ ክፍያ ወጣቶች ላይ ትኩረት ለማድረግ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ በተለያዩ ክለቦች ሲፈለግ ቆይቶ በመጨረሻ ፈረሰኞቹን ተዋህዷል፡፡ የ26 አመቱ ተጫዋች […]

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ።

ልዑኩ ወደ ሀገር ቤት የመጣውም በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መካከል ባሳለፍነው ነሃሴ 1 2010 ዓ.ም የእርቅ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ነው። ልዑኩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም የኦህዴድ የከተማ ፖለቲካና የድርጅት ዘረፍ ሀላፊ አቶ ከፍያለው አያና እናሌሎች የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውለታል። የልዑካን ቡድኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ አስፈጻሚ […]

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንድነት ላይ ያተኮሩ በዓላትን ላዘጋጅ ነዉ አለ፡፡

ከነሐሴ አጋማሽ አስከ መስከረም 30 የሚቆየዉ የበዓላት ዝግጅት “አንድ ሆነን አንድ እንበል” በሚል መሪቃል የሚከበር ነዉ፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የሚዘጋጁት የተለያዩ በዓላት ለአዲስ አመት የሚመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ቱሪስቶችን መቀበል ላይ ያተኮረ ነዉ ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ በሆቴሎች በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በአስጎብኚ ድርጅቶች ያገልግሎት ዋጋ ቅነሳ በተጨማሪ ሁላችንም ኢትዮጵያዉን ፤ኢትዮጵያዊ በሆነ […]

የዘንድሮ የኢ.ቢ.ሲ የስፖርት ሽልማት በመጪው መስከረም በሸራተን አዲስ እንደሚደረግ ይፋ ሆነ፡፡

በ 2009. ዓ.ም የተጀመረው የኢ.ቢ.ሲ የአመቱ ምርጥ የስፖርት ሽልማት በዘንድሮ አመትም ለሁለተኛ ጊዜ በአምስት ዘርፎች እንደሚያካሄድ ኮርፖሬሽኑ አስታዉቋል፡፡ የኢ.ቢ.ሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አቤል አዳሙ ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ጋር ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት በእግር ኳስ ዘርፍ እና በአትሌትክስ ዘርፍ በሁለቱም ፆታዎች ፤ከአምናው በተለየ ደግሞ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ዘርፍም በዘንድሮዉ ሽልማት ተካቷል፡፡ እነዚህን እጩዎች […]