በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን አሉ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ፡፡
አርትስ 18/12/2010 የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ልኡካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ኮንግረንስማን ክሪስ ስሚዝ አሁን እየተካሄደ ያለው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ዕድገት ለምታደርገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀው […]