loading
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዎንግ ዩ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር ተወያዩ

በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙትን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሁለቱ የሃገሪቱ ታላላቅ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የጠበቀ የረጅም ጊዜ ግንኙነት እና ቻይና ለኢትዮጵያ በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያ ተነጋግረዋል። ዋንግ ዩ ከጠቅላይ ሚኒስትር […]

አስተዳደሩ ከ134 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ አቅዷል

አስተዳደሩ ከ134 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ አቅዷል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንዳሉት ቤቶቹ የሚተላለፉት በሚቀጥሉት 8 ወራት ውስጥ ነው። ምክትል ከንቲባው ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 6ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የ2011 በጀት ዓመት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው። ምክትል […]

ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ የብረት ምርቶች ለህገ ወጥ ስራ እየዋሉ ነው ተባለ

  በኢንቨስትመንት ስም ከቀረጥ ነፃ ወደኢትዮጵያ የሚገቡ የብረት ምርቶች ለህገ ወጥ ስራ እየዋሉ በመሆኑ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ከፍተኛ ገንዘብ እያሳጣው መሆኑን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። የብረት ምርት ፍላጎት በከፍተኛ መጠን ባደገባት ኢትዮጵያ መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በሆቴሎች እና መሰል ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ብረት ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ፈቅዷል። ነገር ግን ይህን የማበረታቻ እድል ባልተገባ ሁኔታ እየተጠቀሙ የሚገኙ […]

በአብዲ መሃመድ ዑመር ላይ የተጀመረው ምርመራ በ14 ቀናት ተራዘመ

በአብዲ መሃመድ ዑመር ላይ የተጀመረው ምርመራ በ14 ቀናት ተራዘመ ፖሊስ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በቀረቡት የሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር ላይ የጠየቀውን ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ችሎቱ ፈቀደ። ችሎቱ የሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ ሙሃመድ ዑመርና ከሳቸው ጋር በመተባበር በተጠረጠሩት ሶስት ተከሳሾች ላይ ባለፉት14 ቀናት የተካሄደውን የምርመራ ውጤት አድምጧል፡፡ […]

የአፍሪካ ህብረት በዚህ ዓመት የአፍሪካ ፓስፖርትን ስራ ላይ አውላለሁ አለ

በአፍሪካ ሀገራት መካከል ነፃ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ ሲባል ህብረቱ በዚህ የፈረንጆች ዓመት የአፍሪካ  ፓስፖርት መመሪያ ማዘጋጀትና ማተም ላይ እንደሚሰራ ይፋ አድርጓል፡፡ ፓስፖርቱን በመጭው የካቲት ወር በአዲስ አበባ በሚካሄደው 32ኛው የህብረቱ ጉባኤ እንደሚበሰር ይጠበቃል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መህመት በአዲስ ዓመት መልዕክታቸው ‹‹ ዓባል ሀገራቱ በአህጉሪቱ የሀገራት ድንበር በቀላሉ ለመግባትና ለመንቀሳቀስ እየወሰዳችሁት ላለው  እርምጃ አባል […]

ሪያድ የካሾጊ ገዳዮች የሞት ቅጣት ይገባቸዋል እያለች ነው

ሪያድ የካሾጊ ገዳዮች የሞት ቅጣት ይገባቸዋል እያለች ነው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊን በመግደል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የፍርድ ሂደት በትናንትናው ዕለት መሰማት ጀምሯል፤  ሳውዲ አረቢያም በጠቅላይ አቃቢ ህግ በኩል ከተጠርጣሪዎች መካከል አምስቱ በሞት እንዲቀጡ ጠይቃለች፡፡ በመንግስት የሚተዳደረው የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው፤ ሪያድ ላይ በዋለው ችሎት አቃቢ ህግ በግድያው ተጠርጥረው በቀረቡት 11 ተከሳሾች ተገቢ ቅጣት እንዲፈርድባቸው የጠየቀ ሲሆን በቀጥታ […]

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ የጥቁር አንበሳ ካንሰር ማዕከልን ጎበኙ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሚገኘው የካንሰር ማዕከል ተኝተው ህክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ህጻናትና ልጆችን ጎበኙ፡፡ ካንሰር በማህበረሰቡ ላይ እያደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመከላከል መላው ህብረተሰብ የሚጠበቅበትን አስተዋጽዎ እንዲጫወትም ፕሬዝደንቷ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚገኘው የካንሰር ማዕከል 42 የሚደርሱ አልጋዎች ብቻ ቢኖሩትም ተቀብሎ የሚያስተናግዳቸው ህጻናትና […]