loading
በኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ሽንፈት ገጥሞታል

በኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ሽንፈት ገጥሞታል በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ የመጨረሻ 16ቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ባርሴሎና ከሜዳው ውጭ በሌቫንቴ የ2 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዶ ተመልሷል፡፡ ኢሪክ ካባኮ እና ቦርያ ማዮራል ለሌቫንቴ በመጀመሪያው አጋማሽ 20 ደቂቃ ውስጥ ያስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች አሸናፊ እንዲሆን አግዘዋል፡፡ ብራዚላዊው አማካይ ፊልፔ ኮቲንሆ በ85ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት የፍፁም ቅጣት ምት ግብ የቡድኑን ከባዶ መሸነፍ […]

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን አቀኑ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን አቀኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴራሊዮን ጉብኝታቸውን የሚያደርጉት ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ነው። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያካሂዱት ከሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ነው ተብሏል። በጉብኝቱ ወቅት ሁለቱ ባለስልጣናት የሴራሊዮን እና ኢትዮጵያን ወዳጅነት […]

በአለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሙሉ ወደአዲስ አበባ ተጠሩ

በአለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሙሉ ወደአዲስ አበባ ተጠሩ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሁሉም የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጥሪ ማድረጉን አስታወቀ። ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት እንደተገኘው መረጃ ለአምባሳደሮቹ ጥሪ የተደረገው በተለያዩ ወቅታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ለማድረግ ተብሎ ነው። አምባሳደሮቹ ወደአዲስ አበባ የሚመጡት በቀጣዩ ሳምንት ነው ተብሏል።

በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የሽግግር ኦነግ አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ተወያዩ

በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የሽግግር ኦነግ አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ተወያዩ በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የኦነግ የአመራር ቡድን መንግስት ያደረገለትን ጥሪ ተከትሎ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰ በኋላ ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝቶ ተወያይቷል። በርዕሰመስተዳድሩ ጽህፈት ቤት በተካሄደው የሁለቱ አካላት ውይይት የኦነግ አመራሮች […]

ገንዳውኃ አካባቢ በመከላከያ አባላት ደረሰ የተባለውን ጉዳት የሚያጣራ ቡድን  በአስቸኳይ እንደሚላክ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታውቀዋል

ገንዳውኃ አካባቢ በመከላከያ አባላት ደረሰ የተባለውን ጉዳት የሚያጣራ ቡድን  በአስቸኳይ እንደሚላክ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታውቀዋል።   ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ገዱ በምዕራብ ጎንደር ዞን የተከሰተውን ችግር አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ማጣራቱ የሚካሄደው ከፌዴራልና ከሚመለከታቸው አካላት በተውጣጣ ቡድን ነው ብለዋል። እንደ ርዕሰመስተዳድሩ አንድ የኮንስትራክሽን ድርጅት መኪኖቹን ከአንደኛው ፕሮጀክት ወደ ሌላኛው ፕሮጀክት ለማንቀሳቀስ በሞከረበት ወቅት […]

የአማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ስራአስፈፃሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል

የአማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ስራአስፈፃሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በክልሉ የህግ የበላይነት ተረጋግጦ ሰላምና መረጋጋት በማስፈን በኩል መሰራት አለባቸው ተብሎ የተማነባቸውን ጉዳዮች በመወያየት ውሳኔ ማሳለፉን የማዕከላዊ ኮሚቴው ፅህፈት ቤት አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር እንዴት በጋራ መስራት እንደሚቻል በዝርዝር በመወያየት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ስራ […]

በኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ዳግም መጀመር የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል አሉ የትግይ ክልል ም/ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን

በኢትዮ–ኤርትራ ግንኙነት ዳግም መጀመር የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል አሉ የትግይ ክልል ም/ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ዶክተር ደብረፂዮን ይህን ያሉት የተጀመረውን የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ለማጠናከር በማሰብ የሁለቱ ሀገራት አጎራባች ህዝቦች በሰቲት ሁመራ ተከዜ ወንዝ ድንበር ላይ በተደረገ ክብረበአል ላይ ነው፡፡ በስነ-ስርዓቱ ላይ  ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንደተናገሩት፥ የተቋረጠው የሀገራቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጀመር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር  […]

ሜጀር ጄኔራል ክንፈን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች ከ319 ሚሊየን ብር በላይ በማባከን ክስ ተመሰረተባቸው

ሜጀር ጄኔራል ክንፈን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች ከ319 ሚሊየን ብር በላይ በማባከን ክስ ተመሰረተባቸው የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩትን ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ በስምንት ግለሰቦች ላይ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ከ319 ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ሲል ክስ መስርቷል፡፡ ስምንቱ ተከሳሾች ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም  ወንጀል ሰባት ክሶች ቀርቦባቸዋል፡፡ በክስ ሰነዱ […]

ላልይበላን በቀንና በማታ መጎብኘት የሚያስችል የአረንጓዴ ብርሃን ቴክኖሎጂ ሊተገበር ነው ተባለ

ላልይበላን በቀንና በማታ መጎብኘት የሚያስችል የአረንጓዴ ብርሃን ቴክኖሎጂ ሊተገበር ነው ተባለ፡፡ ከፍተኛ የቱሪዝም ፍሰትን የሚጨምር ነው የተባለው ይኸው ቴክኖሎጂ ተግባራዊ የሚደረገው ከአየር ላንድ መንግስት ጋር በመተባበር ነው። የአየር ላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናትን በጎበኙበት ወቅት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንዳሉት ቴክኖሎጂው በአክሱም ፣ሐረር እና አዲስ አበባ ላይ ተግባራዊ ይደረጋል። የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር እንደተናገሩት አየር ላንድ […]

የካቶሊክ  ቤተ ክርስቲያን የኮንጎን የምርጫ ውጤት እየሞገተች ነው

የካቶሊክ  ቤተ ክርስቲያን የኮንጎን የምርጫ ውጤት እየሞገተች ነው፡፡ የኮንጎን የምርጫ ሂደት ከታዘቡት ተቋማት መካከል በሀገሪቱ ትልቅ ተሰሚነት ያላት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አንዷ ናት፡፡ ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያኗ የምርጫው ውጤት ሲገለፅ አሸናፊው እና እርሷ የታዘበቸው እውነታ እንዳልተገጣጠመላት በይፋ ተናግራለች፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የአፍሪካ ህብረት እና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ታዛቢዎችም የቤተ ክርስቲያኗን ሀሳብ ይጋራሉ፡፡ ነገር ግን […]