loading
የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ዋሽንግተን ሊያቀኑ ነው

የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ዋሽንግተን ሊያቀኑ ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ እና የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ዮንግ ኮል ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ወደ ዋሽንግተን ከሚጓዙት የፒዮንግያንግ  ባለስልጣናት መካከል ከአሜሪካ ጋር የኮሪያን ልሳነ ምድር ከኒውክሌር ስጋት ነፃ ለማድረግ የሚደራደሩት ይገኙበታል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማቶች በዚህ መልክ ተገናኝተው መነጋገራቸው ኪም እና ትራምፕ በቀጣዩ ጊዜ […]

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር የሚመራበት ረቂቅ ደንብ ፀደቀ

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር የሚመራበት ረቂቅ ደንብ ፀደቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጋር በቀጣይ የሚያደርጉት ውይይትና ድርድር የሚመራበት 16 አንቀጽ ያለው ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይተው ማፅደቃቸውን፣ በውይይቱ ከተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማወቅ መቻሉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ፓርቲዎቹ ከዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት በጉዳዩ ላይ በጋራ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ በውይይቱ […]

ኢትዮጵያና ቱርክ በባህልና በቅርስ ጥበቃ ዘርፍ በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ

ኢትዮጵያና ቱርክ በባህልና በቅርስ ጥበቃ ዘርፍ በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ ይህ የተባለው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳሁን የተመራ የልዑካን ቡድን ከቱርክ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ሰርዳር ካም ጋር አንካራ ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ ሁለቱ አገራት በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ትብብራቸውን ይበልጥ በማጠናከር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። በዚህ ወቅት ዶ/ር ሂሩት የቱርክ የትብብር ኤጀንሲ በኢትዮጵያ […]

ምንጋግዋ ፑቲንን ሀገሬን ለማልማት ቀኝ እጅዎን ያውሱኝ እያሏቸው ነው

ምንጋግዋ ፑቲንን ሀገሬን ለማልማት ቀኝ እጅዎን ያውሱኝ እያሏቸው ነው፡፡ የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የፑቲንን ድጋፍ ፍለጋ ባለስልጣኖቻቸውን አስከትለው ሞስኮ ገብተዋል፡፡ በሀገር ቤት በዋጋ ንረት ሳቢያ  የተቃውሞ ሰልፍ ረፍት የነሳቸው ምናጋግዋ ክሬምሊን ከገቡ በኋላ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ሀገሬ ከኢኮኖሚ ችግር ትላቀቅ ዘንድ እንደታላቅ ወንድም አቅፈው ደግፈው እንዲያግዙኝ አፈልጋለሁ ብለዋቸዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሩሲያን ጨምሮ […]

የአሜሪካ ፖሊስ ለኢራን ቲሌቭዥን የምትሰራዋን ጋዜጠኛ አስሯታል

የአሜሪካ ፖሊስ ለኢራን ቲሌቭዥን የምትሰራዋን ጋዜጠኛ አስሯታል ሮይተርስ ፕሬስ ቴሌቭዥንን ጠቅሶ እንደዘገበው ባልታወቀ ምክንያት የአሜሪካ ፖሊስ ጋዜጠኛዋን ሴይንት ሉዊስ በሚገኘው ላምበርት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው በቁጥጥር ስር ያዋላት፡፡ በትውልድ አሜሪካዊት በዜግነት ደግሞ ኢራናዊት የሆነቸው ማርዜይ ሀሺሚ በኢራን መንግስት ለሚተዳደረው ፕሬስ ቴሌቭዥን መስራት ከጀመረች ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡ ሀሺሚ ወደ አሜሪካ ያቀናቸው የታመመ ወንድሟን ለመጠየቅ እንደነበር እና […]