loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኳታር ገብተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኳታር ገብተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን ዶሃ ሲደርስ የኳታር የትራንስፖርት እና መገናኛ ሚኒስትር ጃሲም ቢን ሳይፍ አል ሱለይቲ አቀባበል አድርገውለታል። በጉብኝታቸውም ከሃገሪቱ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር በሁለትዮሽና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ባለፈም በሁለትዮሽ ትብብር እና  የልማት ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ […]

በምዕራብ ወለጋ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ

በምዕራብ ወለጋ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ሁምነ ዋቀዮ ተብሎ የሚጠራው ቀበሌ ውስጥ   ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 5 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሶስቱ የኢትዮጵያ ዜጎች ሲሆኑ፣ ሁለቱ ደግሞ የውጭ ዜጎች መሆናቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡  

ኢትዮጵያ ለቶጎና ቻድ በሲቪል አቪየሽን ዘርፍ ድጋፍ ልታደርግ ነው

ኢትዮጵያ ለቶጎና ቻድ በሲቪል አቪየሽን ዘርፍ ድጋፍ ልታደርግ ነው ኢትዮጵያ በቅርቡ ለቶጎና ቻድ በሲቪል አቪየሽን ዘርፍ ድጋፍ ልታደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን አስታወቀ። የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር ኮሌኔል ወሰንየለህ እንዳሉት ድርጅቱ የኢትዮጲያ አየር መንገድ አገልግሎት ጥራትን ከማስጠበቅ ባሻገር ለተለያዩ ሀገራት በሲቪል አቪየሽን ዘርፍ ድጋፍ እያደረገ ነው። በዚህ መሰረትም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ለጅቡቲ፣ሱዳን፣ ማላዊ እና […]

ኒው ዚላንድ ከሀዘኗ መፅናናት ተስኗታል፡፡

ኒው ዚላንድ ከሀዘኗ መፅናናት ተስኗታል፡፡ በዚህች ሀገር  የተከሰተው በታሪኳ ታይቶ የማያውቀው የጅምላ ግድያ የብዙዎቹን ልብ በመሪር ሀዘን ሰብሯል፡፡ ይህ በሙስሊሞች ላይ የተፈፀመው ግድያ ሳያንስ የሟቾቹ የቀብር ስነስርዓት መዘግየቱ ለቤተሰቦቻቸው ሌላ ተጨማሪ ሀዘን ሆኖባቸዋል፡፡ በሙስሊሞች ደንብ መሰረት አንድ ሰው በሞተ በ24 ሰዓት ውስጥ መቀበር አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ፖሊስ የሟቾቹን ማንነት ለይቸ አላጠናቀቅኩም በማለቱ ምክንያት እስካሁን ቤተሰቦቻቸውን […]