loading
የብሔራዊ ቡድኖች የወዳጅነት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ

በዛሬው ዕለት ሁለት ግጥሚያዎች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡ ምሽት 4፡45 ጀርመን በወልፍስቡርግ ቮልስዋገን አሬና ላይ ሰርቢያን ታስተናግዳለች፡፡ በአሰልጣኝ ዩአኪም ሎው የሚመራው የጀርመን ቡድን በብራዚል የተሰናዳውን የዓለም ዋንጫ ቢያሳኩም፤ በሩሲያው መሰናዶ ገና በጊዜ ነበር የተሰናበቱት፤ በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ውድድርም ቢሆን አልሆነላቸውም፡፡ ከውጤት ማጣት ጉዞዎች በኋላ ጀርመን የዩሮ 2020 የማጣሪያ ውድድሯን ከመጀመሯ አስቀድሞ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ታደርጋለች፡፡ የማንችስተር ሲቲው አማካይ […]

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ቢን ናስር ቢን ካሊፋ አል ታሃኒ ጋር ተወያዩ

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ቢን ናስር ቢን ካሊፋ አል ታሃኒ ጋር ተወያዩ፡፡ በኳታር ይፋ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከሀገሪቱ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ  ከጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ቢን ናስር ቢን ካሊፋ አል ታሃኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ካላት ትልቅ ሚና […]

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዘመናዊ የከፍያ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እየደረግኩ ነው አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዘመናዊ የከፍያ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እየደረግኩ ነው አለ። አዲሱ አሰራር ደንበኞች የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸው በዘመናዊ መንገድ ለመፈፀም የሚያስችላቸው ነው ተብሏል። ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ተግባራዊ ይሆናል በተባለው በዚሁ አዲስ የክፍያ አሰራር ተጠቃሚ የሚሆኑት የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ማለትም ሁሉም የኢንዱስትሪ ደንበኞች፣ የግል ድርጅቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሲሆኑ፤በተጨማሪም ማንኛውም […]

በህፃናት ላይ የሚያጋጥሙ የካንሰር ህመሞችን ለማከምና ለመከላከል የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ በኢትዮጵያ እና በአጋር አካላት መካከል ተፈረመ

በህፃናት ላይ የሚያጋጥሙ የካንሰር ህመሞችን ለማከምና ለመከላከል የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ በኢትዮጵያ እና በአጋር አካላት መካከል ተፈረመ፡፡ ስመምነቱ በህፃናት ላይ የሚያጋጥሙ የኦንኮሎጂና ኬማቶሎጂ የካንሰር አይነቶችን ለማከም፣ ለመከላከልና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ለህክምና ባለሙያዎች መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡   ስምምነቱን የተፈራረሙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ሊያ ከበደ፣ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ይርጉ ገ/ህይወት እንዲሁም […]

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ለህግ ለታራሚዎች 17 ሚሊየን 220 ሺህ ብር የሚገመት የአልባሳት  ድጋፍ አደረገ

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ለህግ ለታራሚዎች 17 ሚሊየን 220 ሺህ ብር የሚገመት የአልባሳት  ድጋፍ አደረገ። ኮሚሽኑ በደቡብ ክልል ማረሚያ ኮሚሽን ሀዋሳ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህግ ታራሚዎች ነው አልባሳቱን የለገሰው። የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ  በስነስርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ሁሉም ዜጋ ተጠቃሚ እንዲሆን ከፀጥታ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ርብርብ […]

አሜሪካ የቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን ፈቃድ ላይ ምርመራ ልታደርግ መሆኑ ተሰማ

አሜሪካ የቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን ፈቃድ ላይ ምርመራ ልታደርግ መሆኑ ተሰማ ሮይተርስ እንደዘገበው የአሜሪካ መንግሥት ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን ለመብረር እንዴት ፈቃድ እንዳገኘ እንዲጣራ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ከመረጃ ሳጥኑ የተገኙት መረጃዎች ለኢትዮጵያዊያን መርማሪዎች የሚሰጥበት የመረጃ ልውውጥ ሂደቱም ቀጥሏል፡፡ በአምስት ወራት ውስጥ ሁለቴ የተከሰከሰው ይህ የቦይንግ ስሪት አውሮፕላን በኢትዮጵያው እና በኢንዶኔዢያው  አደጋዎቹ ውስጥ የቴክኒክ ችግር […]

ላሊበላን ለመጠገን በፈረንሳይ መንግስት የተገባው ቃል አሁን ድረስ ተግባራዊ መሆን አልጀመረም

ላሊበላን ለመጠገን በፈረንሳይ መንግስት የተገባው ቃል አሁን ድረስ ተግባራዊ መሆን አልጀመረም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ቅርሶች በመፍረስ አደጋ ውስጥ ስለሆኑ አፋጣኝ ጥገና ያስፈልጋቸዋል ተብሎ ከፍ ያለ እንቅስቃሴ ተጀምሮ ነበር። የአካባቢው ህዝብም ይህ ቅርስ ተረስቷል፣ እናድነው ብሎ ጉዳዩን መነጋገሪያ ለማድረግ ሰላማዊ ሰልፍ እስከመውጣት ደርሶ ነበር። አርትስ ቲቪ በቦታው ተገኝቶ ይህንኑ ጉዳይ ዘግቦ ነበር፡፡ የፈረንሳይ መንግስት ቅርሶቹን ለማደስ […]

ዋሊያ ቢራ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ56 ሚሊዬን ብር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ

የዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማህበር ለአራት ዓመታት የሚዘልቅ የ56 ሚሊዬን ብር የስፖንሰርሽፕ (አጋርነት) ስምምነት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ፈፅሟል፡፡ ስምምነቱ በፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ እና በሃይንከን ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዩጂን ዩባሊጆሮ መካከል በካፒታል ሆቴል ሲከናወን፤ በየዓመቱ 14 ሚሊዬን ብር ታሳቢ የሚሆን በወንዶች ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ላይ ተፈፃሚ ይሆናል […]