መረጃዎች የአውሮፕላን አደጋውን መንስኤ በተመለከተ ወደ ቦይንግ እየጠቆሙ ነው
መረጃዎች የአውሮፕላን አደጋውን መንስኤ በተመለከተ ወደ ቦይንግ እየጠቆሙ ነው። ብዙ ተስፋ የተጣለበት እና ለምርመራ ወደ ፈረንሳይ የተላከው የመረጃ ሳጥንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ከኢንዶኔዢያው ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው የሚያሣይ መረጃ አቀብሏል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት ከሆነውና ቢሾፍቱ አቅራቢያ ከወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን ስብርባሪ ውስጥ የመረጃ መዝጋቢ ሳጥን(ብላክ ቦክስ) መገኘቱ የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ሲቃትቱ ለነበሩ ልቦች ሁሉ እፎይታን አስገኝቷል። ይህ ሳጥን በዚህ ፍጥነት ሊገኝ መቻሉ በአደጋው ዙሪያ የሚሰነዘሩ መላምታዊ መረጃዎችን በማስቀረት ሳይንሳዊ […]