loading
ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያገናኙት ሁሉም የድንበር በሮች መዘጋታቸው ተሰማ

ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያገናኙት ሁሉም የድንበር በሮች መዘጋታቸው ተሰማ ተዘጉ የተባሉትና አራቱ ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያገናኙት ድንበር በሮች ዛላምበሳ-ሰርሃ ፣ራማ-ክሳድ ዒቃ፣ ሁመራ-ኦምሃጀር  እና ቡሬ-ደባይ ሲማ ናቸው፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ተዘጋ የተባለውን የሁመራ-ኦማሃጀር ድንበር በር ተከትሎ ሰኞ ሚያዝያ 14 ቀንም የቡሬ-አሰብ ድንበርም በተመሳሳይ  መዘጋቱ ተሰምቷል፡፡ የተቀሩት ሁለቱ ድንበሮች ደግሞ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት መዘጋታቸው ታውቋል። ከኤርትራ ወገን […]

ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከተጓጓዙ ከ29 ሚሊየን በላይ መንገደኞች 87 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ተገኝቷል- የትራንስፖርት ሚኒስቴር

ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከተጓጓዙ ከ29 ሚሊየን በላይ መንገደኞች 87 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር መገኘቱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።   የክፍያ ጉዳናዎችን በተመለከተም የክፍያ መንገድ ኢንተርፕራይዝ ባለፉት 9 ወራት 6 ሚሊየን 38 ሺህ 800 ተሽከርካሪዎችን ምልልስ በማስተናገድ ከ191 ነጥብ 4 ሚለየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተነግሯል። የትራንስፖርት ሚኒስቴር የ9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን […]

የምግብ ዘይት በማምረት የሚታወቀው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የማሌዥያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነው

የምግብ ዘይት በማምረት የሚታወቀው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የማሌዥያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነው   ኩባንያው በኢትዮጵያ የምግብ ዘይት ምርት ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ለኩባንያው ሀላፊዎች በዘርፉ ባለው የኢንቬስትመንት እድል ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ። በኢትዮጵያ ያለው የምግብ ዘይት ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም 90 በመቶ የሚደርሰው ምርት ከውጭ አገራት በግዢ የሚገባ […]

በሶስት የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች 990 ሺህ ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

በሶስት የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች 990 ሺህ ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ግምታቸው 989,800 ብር የሆኑ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአርበረከቴ ፣ በቶጎጫሌ እና  በሐረር የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች  ነው።   አርበረከቴ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በአህዮች ተጭኖ ሲጓጓዙ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኮንትሮባንድ እቃዎች መድሃኒት፣ መነፅርና አልባሳት ሲሆኑ በቶጎጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ደግሞ […]

የጅቡቲ-ገላፊ እና የታጁራ-በልሆ መንገዶች ግንባታ እየተፋጠነ ነው

የጅቡቲ-ገላፊ እና የታጁራ-በልሆ መንገዶች ግንባታ እየተፋጠነ ነው የጅቡቲ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሞሃመድ አብዱልካድር የጅቡቲ-ገላፊ እና የታጁራ-በልሆ መንገዶች ግንባታን አስመልክቶ ከተቋቋመው የአገሪቱ የቴክኒክ ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ለአሽከርካሪዎች አስቸጋሪ መንገድ የሆነውን የዲኪል-ጋላፊ መንገድ እንዲሁም የታጁራ-በልሆ መንገድ ግንባታን አስመልክቶ ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን በጥናቶቹ መሰረት የዲኪል-ገላፊ መንገድ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጨረታ በማውጣት ወደ ስራ የሚገባበት መንገድ ተጠቁሟል፡፡ […]