የስፔን ላሊጋ የ33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ
ዛሬ ምሽት 4፡00 ላይ ዲፖርቲቮ አላቬስ በሜዳው ሪያል ቫያዶሊድን ይገጥማል፡፡ በነገው ዕለት ደግሞ ምሽት 3፡ 45 ላይ ባርሴሎና በካምፕ ኑ ሪያል ሶሴዳድን ያስተናግዳል፡፡ የዲዬጎ ሲሞኔው አትሌቲኮ ዴ ማድሪድ ወደ ኤይባር ተጉዞ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ ሴልታ ቪጎ ከ ጂሮና እና ራዮ ቫዬካኖ ከሁሴካ በዕለቱ የሚደረጉ ሌሎች ግጥሚዎች ናቸው፡፡ የሳምንቱ ጨዋታዎች ዕሁድ ሲቀጥሉ ሪያል ማድሪድ በሳንቲያጎ ቤርናባው […]
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ። በዚሁ መሰረት ቀድሞ የኦዲፓ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩትን ዶ/ር አለሙ ስሜን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቀድሞ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ጃንጥራር አባይን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ቀድሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰመስተዳድር […]
ጋህነን የትጥቅ ትግሉን ትቶ ወደሃገሩ ገባ
በኤርትራ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ሀገሩ ገባ። የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) መቀመጫውን ኤርትራ በማድርግ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ ዓመታትን አስቆጥሯል። የንቅናቄው አባላትና አመራሮች ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ደጋፊዎቻቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል። የንቅናቄው ሊቀመንበር አቶ ኡኬሎ […]
በሳዑዲ አረቢያ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደሃገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ አረቢያ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደሃገራቸው ተመለሱ ። እነዚሁ 850 ኢትዮጵያውያን በሁለት ዙር ባሳለፍነው ሳምንት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ከተመለሻቹ መካከል 445 ያህል ሰዎች ባሳለፍነው አርብ፣ ቀሪዎቹ 405 ደግሞ እሁድ እለት ወደሀገራቸው የገቡ ናቸው። ከስደት ተመላሾቹ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በራሳቸው ፈቃድ ሲሆን ሳዑዲ አረቢያ የገቡትም ቀይ ባህርን አቋርጠው በህገ-ወጥ መንገድ እንደነበር ተነግሯል። ተመላሾቹ ወደ ሀገራቸው […]
“ዘላቂ ሰላም የሚገኘው በህዝቡ ያላሳለሰ ጥረትና ትጋት እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በሚኖር መቀናጀት ነው” ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም የሚገኘው በህዝቡ ያላሳለሰ ጥረትና ትጋት እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በሚኖር መቀናጀትና መደጋገፍ መሆኑን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል አስገነዘቡ። በሰሜን እዝና በትግራይ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ የሰላምና የደህንነት ኮንፈረንስ ተካሂዷል። የትግራይ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አመራሮች ጋር የጋራ የሰላምና የደህንነት ኮንፈረንስ ባካሄዱበት […]