loading
የደንበጫው “የካናቢስ ፋብሪካ” ግንባታ እቅድ አነጋጋሪ ሆኗል

የደንበጫው ካናቢስ መድሃኒት ፋብሪካ እቅድ አነጋጋሪ ሆኗል። በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ወረዳ ሊገነባ ነው የተባለው የካናቢስ መድሃኒት ፋብሪካ ፍቃድ የሰጠው አካል የለም ተባለ። የደምበጫ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽህፈትቤት በፌስቡክ ገጹ የካናቢስ መድሃኒት ፋብሪካ በወረዳው ሊገነባ መሆኑን በመግለጽ ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያሰራጨው ደብዳቤ እና የሰራው ዘገባ በማህበራዊ ሚዲያ ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል። ጽህፈት ቤቱ አስቀድሞ […]

የአየር ላንድ መንግስት ቅርሶችን በአረንጓዴ ብርሃን ማስዋብ በሚል በላሊበላ የአረንጓዴ ብርሃን ዝግጅት አካሄደ

የአየር ላንድ መንግስት ቅርሶችን በአረንጓዴ ብርሃን ማስዋብ በሚል በላሊበላ የአረንጓዴ ብርሃን ዝግጅት አካሄደ፡፡ ዝግጅቱ ቅርሶችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ተብሏል። ያም ሆኖ የአንድ ምሽቱ ተግባር ከዚህ ቀደም ከተያዘውና ላሊበላን በዘላቂነት ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ከተባለው ፕሮጀክት ጋር አልገናኝ ማለቱ ለብዙዎች ጥያቄ ፈጥሯል ። የአርትስ ሪፖርተር ከስፍራው ያጠናቀረችው ዘገባ እንደሚያስረዳው። በያዝነው ወር አየርላንድ እና ኢትዮጵያም […]

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ላሉ 170ሺህ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ያግዛል  የተባለ የ2 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ጸደቀ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ላሉ 170ሺህ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ያግዛል  የተባለ የ2 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ጸደቀ።   ፈንዱን ያጸደቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ ለወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ለመመደብ የቀረበ ረቂቅ ሰነድ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡   በዚህም መሠረት ዝርዝር ዕቅዶችን በማዘጋጀት እና ከወጣቱ ጋር ሰፊ የምክክር መድረኮችን በማዘጋጀት የጋራ […]

የጌዲዮ ተፈናቃዮች ከገቢዎች ሚኒስቴር የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አገኙ

የጌዲዮ ተፈናቃዮች ከገቢዎች ሚኒስቴር የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አገኙ።   የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በትናንትናው ዕለት ከምዕራብና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም ጌዲኦ ዞን አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች የተጠለሉበት ቦታ በመገኘት ነው ከ21 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ያደረጉት። ለተፈናቃዮች የተደረገው ድጋፍ  ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለተጎጂዎች እንዲደርስ ለማስቻል የተፈናቃይ ተወካዮችና የዞኑ አመራሮች በተገኙበት ገደብ ከተማ ላይ […]

ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ እያደገ ነው ተባለ

ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ እያደገ ነው ተባለ።   በቻይናውያን ዘንድ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል የተባለው ይኸው የኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ በሃገሪቱ በተካሄደ ዓለም ዓቀፍ ልዩ የቡና ትርኢት ቀርቧል።   ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ይኸው አውደትርዒቱ ከመጋቢት 2 እስከ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በቻይና ፑኤር ከተማ ተካሂዷል። እንደ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት  ገለፃ […]

በታንዛንያ እስር ቤት የነበሩ 235 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው

በታንዛንያ ታንጋ በሚባል ከተማ በሚገኝ ማዌይኒ በሚባል እስር ቤት የነበሩ 235 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅኅፈት ቤት አስታውቋል። ስደተኞቹን ኢትዮጵያውያን የመመለሱን ስራ  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሄራዊ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከታንዛንያ መንግስት ጋር በመተባበር እየሰራ ነው ተብሏል። ከ3 ቀናት በፊት በተመሳሳይ ቦታ የነበሩ 50 […]