loading
የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል:: ማሊ ማእቀቡ የተጣለባት ባለፈው ወር በፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ነው፡፡ መፈንቅለ መንግስቱ ከተካሄደ በኋላ ሀገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ሲካሄድ የነበረውን ድርድር በበላይነት የመራው ኢኩዋስ ማእቀቡ ይነሳ አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ለመወሰን ለዓርብ […]

ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች:: በዓሳ ሀብት ልማት ተቋም ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ግለሰብ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ደብዛቸው ጠፍቶ እንደነበር የገለፀችው ሴኡል በመጨረሻ በሰሜን ኮሪያ የባህር ጠረፍ አስከሬናቸው መገኘቱን አረጋግጣለች፡፡ የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ሰውየውን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተኩሰው ገድለው ሲያበቁ በጭካኔ አስከሬናቸው […]

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ሂደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ሂደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለፀ:: ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ2013 በጀት ዓመት ለማከናወን ባቀዳቸው ተግባራትና በአስር አመት መሪ እቅዱ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። በመድረኩም የህግ አወጣጥና አተገባበር፣ የሰብአዊ መብትና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል። በጠቅላይ አቃቤ ህግ […]

የምስራቅ ሐረርጌ አገረ ስብከት የመስቀል በዓል የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንደሚያከብር አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 የምስራቅ ሐረርጌ አገረ ስብከት የመስቀል በዓል የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንደሚያከብር አስታወቀ:: በሐረሪ ክልል የደመራና የመስቀል በዓልን ሐይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በአንድነትና እርስ በርስ በመደጋገፍ በጥንቃቄ እንደሚከበር ነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽህፈት ቤት የገለፀው። የምስቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽህፈት ቤት የትምህርትና ስልጠና ክፍል ሃላፊ መልዓከ […]

አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች። በበርካታ የትያትርና ፊልም ስራዎች የምትታወቀው አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።ለሳምንታት በህመም ላይ የነበረችው አርቲስቷ ዛሬ ማለዳ ነው ማረፏ የተሰማው።የአርቲስቷ ስርዓተ ቀብር ነገ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል።

የሱዳን ናሽናል ኡማ ፓርቲ የአረብ እስራኤል ዲፕሎማሲ ሰላምን ለማምጣት አስተዋፅዖ የለውም ሲል አጣጠለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 የሱዳን ናሽናል ኡማ ፓርቲ የአረብ እስራኤል ዲፕሎማሲ ሰላምን ለማምጣት አስተዋፅዖ የለውም ሲል አጣጠለ:: የፓርቲው መሪ የቀድሞው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አልመሃዲ እስራኤል ከአረቡ ዓለም ጋር የጀመረችውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት መደገፍ እጅ እንደመስጠት ይቆጠራል ብለዋል፡፡ ኖርማላይዜሽን በሚል አዲስ ታክቲክ እስራኤል የጀመረችው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ሰላምን ከማምጣት ይልቅ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ መስፈፀሚያ ነው ሲሉም […]

የማሊ ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 የማሊ ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ:: የሽግግር ወቅቱ ፕሬዚዳንቱ ባህ ንዳዉ የሀገሪቱ ጠቅላይሚኒስትር አድርገው የሾሙት የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞክታር ኡኔን ነው፡፡ የማሊ የሽግግር መንግስት ሲቪል ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሙ ከምእራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ የተጣለበትን ማዕቀብ ለማላላት ሁነኛ መንገድ ሊሆንለት ይችላል ተብሏል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የማሊ ጄኔራሎች ፕሬዚዳንት ቡበከር […]

በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም እንደሚገባ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም እንደሚገባ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታዉቀዋል። ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም በመጠናቀቁ እና የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ […]

በዞኑ 285 የዳስ መማሪያ ክፍሎች በህንጻ ግንባታ ተለወጡ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 በዞኑ 285 የዳስ መማሪያ ክፍሎች በህንጻ ግንባታ ተለወጡ::በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን 285 የዳስ መማሪያ ክፍሎች ወደ ህንጻ ግንባታ መለወጣቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።በሰሜን ወሎም ከ56 ሚሊዮን ብር ባላይ ወጭ የተገነቡ ትምህርተ ቤቶች ለአገልግሎት መዘጋጀታቸው ተነግሯል ። የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ትምህርት መምሪያ የግንባታ መሃንዲስ አቶ አራጋው አዲሱ ለኢዜአ […]

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ንብረታቸውን ላጡ አሰሪዎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2013  በፀጥታ ችግር ሳቢያ ንብረታቸውን ላጡ አሰሪዎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ :: የድጋፍ ማሰባሰቢያው ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተነሳው ሁከት ለዓመታት ሰርተው ያፈሩት ሀብትና ንብረታቸው የወደመባቸውን አሰሪዎች መልሶ ሟቋቋሚያ ነው ተብሏል።”አሰሪው ለአሰሪው” የተሰኘው ይህ መርሃ ግብር የአገሪቷን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል፣ ማኅበራዊ መረጋጋት ለመፍጠርና ስራ ፈጣሪዎችን መልሶ ለማቋቋም […]