የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ::
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ:: የትምህርት ሚኒስቴር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና፣ በጥበብና ሂሳብ ዘርፍ የሚቀርቡ የተማሪዎችን የፈጠራ ስራዎች ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ መመሪያው ተወዳዳሪዎች በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡና አሸናፊዎች በማያሻማ መልኩ ተለይተው ተገቢውን ማበረታቻ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑ ነው […]