loading
የፕሮፌሰር ምትኩ በላቸዉ ስንብት በወንጪ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 የፕሮፌሰር ምትኩ በላቸዉ የስንብት ፕሮግራም በወንጪ ተካሄደ፡፡በወንጪ ኃይቅ አካባቢ የሚኖሩ የማሃበረስብ አባላት በፕሮፌሰር ምትኩ በላቸዉ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸዉን ሀዘን በባህላዊ ለቅሶ ስነስርአት ገልጸዋል፡፡ የባህላዊ ስንብት ስነ ስርዓቱ የተከናወዉ በወንጪ ኃይቅ ዳር በተመሰረተና እሳቸዉ የመጽሐፍት ቤት ባስገነቡበት ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ነዉ፡፡ በዕለት ከተከናወኑት ባህላዊ የሀዘን መግለጫ ስነስርዐቶች ዉስጥ ነዉ፡፡በዕለቱ […]

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚወዳደሩበትን የምርጫ ወረዳ ፓርቲዉ አሳታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚወዳደሩበትን የምርጫ ወረዳ ፓርቲዉ አሳታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ላማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በተከታታይ በፌስቡክ ገጹ እጩዎቹን እያሰተዋወቀ ሲሆን ፤ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ወረዳ 23 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ መሆናቸዉን አስታዉቋል፡፡ የምርጫ ወረዳ 23 የሚያጠቃልላቸው አካባቢዎች ከሳርቤት ቄራ ድልድይ ወንዙን ይዞ ከአፈሪካ ህብርት በታች፤ […]

የአዲስ አበባ ምርጫ ለምን ዘግይቶ ይካሄዳል ?

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013  6ተኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 28 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን የአዲሰ አበባ ከተማ አሰተዳደር ምርጫ ደግሞ ሰኔ 5 መካሄዱ ጥያቄ ማስነሳቱ ይታወቃል፡፡ ይህንን የመራጮች ድምጽ መስጫ ቀን ልዩነትን በተመለከተ አርትስ ቴሌቭዥን ምርጫ ቦርድን ጠይቋል፡፡ የከተማ መስተዳድሮች እና ክልሎች የምርጫ ክልሎቻቸውን የመወሰን ስልጣን የከተማ መስተዳድሮች እና የክልሎች በመሆኑ የአዲስ አበባ […]

አብን የአማራ ህዝብ ጨቋኞችን በካርድ ሊቀጣ ይገባል አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 ሕዝባችን ሰላማዊ እምቢተኝነቱን የቀጠለ ሲሆን የምርጫ ካርድ በማውጣትና ለአብን ድምጹን በመስጠት ጨቋኞቹን ሊቀጣ ይገባል ሲል ፓርቲዉ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣዉ መግለጫ ገልጿል፡፡ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የተደራጀና የተቀናጀ የዘር ፍጅት በማውገዝ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ታላቅ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል ያለዉ ፓርቲዉ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞየአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ […]

ለሁለት አዲስ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶች ለወጣው ጨረታ 6 ዓለም ዓቀፍ የቴሌኮም ድርጅቶች ሰነድ አስገቡ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 ለሁለት አዲስ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶች ለወጣው ጨረታ 6 ዓለም ዓቀፍ የቴሌኮም ድርጅቶች ሰነድ አስገቡ፡፡ የጨረታ ማስገቢያው ጊዜ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ ተጠናቋል። በዚህም ለሁለቱ አዲስ የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶች ሳፋሪኮም ከኬንያ ፣ቮዳፎን ከብሪታኒያ ፣ቮዳኮም ከደቡብ አፍሪካ፣ ሲዲሲ ግሩፕ ከብሪታኒያ፣ ሰሚቶሞ ኮርፖሬሽን ከጃፓን እና ኤምቲኤን ግሩፕ ከደቡብ አፍረካ ሰነዶቻቸውን ማስገባታቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። […]

የአዲስ አበባ የወሰን እና ማንነት ጉዳይ በተመለከት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዚማ) የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ (አነን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ለዲሞክራሲ ክርክር አድርገዋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 የአዲስ አበባ የወሰን እና ማንነት ጉዳይ በተመለከት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዚማ) የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ (አነን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ለዲሞክራሲ ክርክር አድርገዋል፡፡በአርተስ ቴሌቪዥን የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ  በመቅረብ ሀሳባቸውን የሰጡት ሶስቱ ፓርቲዎች አዲስ  አበባን  በተመለከተ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያሉባት ከተማ መሆኗን በመግለፅ በተለይም  ከመልካም አስተዳደር እና ከፍተኛ  የሆነ የስራ አጥ […]

ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረዉ ገጀራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013  ሀሰተኛ ሰነድን ተጠቅሞ ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረው የእጅ ገጀራ ተያዘ የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ከ15 ቀን በፊት በአስመጪ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ አንድ መቶ 86 ሺህ 240 የሆነ የእጅ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ተጓጉዞ ከደረሰ በኃላ ተይዟል፡፡ እቃው ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ […]