loading
በአብዬ በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ ለተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ- 19 ክትባት ተሰጣቸው፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013  በአብዬ በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ ለተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ- 19 ክትባት ተሰጣቸው፡፡ በሱዳን አብዬ ግዛት የሚገኙት የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስለባሪ ሻለቃ አባላት አስትራዜኒካ የተባለው የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ነው የተሰጣቸው፡፡ የሻለቃው የህክምና ሃላፊ ሻለቃ ፀሃይ በላቸው ሰራዊቱ እራሱን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል የተሰጠውን አገራዊና […]

ማኅበረሰቡ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳበ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 ማኅበረሰቡ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳበ፡፡ ኢንስቲትዩቱ በህንድ የተከሰተው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ አሳሳቢ እየኾነ መምጣቱን በማስታወስ ማህበረሰቡ እንዳይዘናጋ አስጠንቅቋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በህንድ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ዓለም አቀፍ ስጋት እየሆነ እንደመጣ መግለጹን ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡ ቫይረሱ እስካሁን በ44 ሀገራት እንደተሰራጨ መገለጹን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል፡፡ […]

በሱዳን በኩል ወደ ሀገር ሊገባ ሲል የተደመሰሰው የህወሃት ቡድን

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 ከሱዳን በመነሳት በማይካድራ አድርገው ወደ ሀገር ሊገቡ የነበሩ 320 የህወሃት ሀይል አባላት ተደመሰሱ፡፡ የህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ሀላፊ ተወካይ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳሉት ይህ ቡድን በማይካድራ ጭፍጨፋ አድርሶ ወደ ሱዳን ሸሽቶ የነበረ ነው፡፡ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ በሰጡት መግለጫ ቡድኑ ዳግም ተደራጅቶ የተለያዩ የመገናኛ መሳሪያዎችንና መድሀኒቶችን በመያዝ ወደ […]