loading
ቴክኖ ታዋቂውን የሆሊውድ ተዋናኝ ክሪስ ኢቫንስን የቴክኖ አለም አቀፍ የንግድ አምባሳደሩ አድርጎ ሾመው::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 ቴክኖ ታዋቂውን የሆሊውድ ተዋናኝ ክሪስ ኢቫንስን የቴክኖ አለም አቀፍ የንግድ አምባሳደሩ አድርጎ ሾመው:: ክሪስ ኢቫንስ በግንቦት 20 በሚደረገው የTECNO የምርት አውደ ርዕይ ላይ የቴክኖ የንግድ አምባሳደር በመሆን የሚቀርብ ሲሆን በሚቀጥሉት የቴክኖ ዓለም አቀፍ የምርት ዘመቻዎች ላይም ቴክኖን በወከል ይሳተፋል:: ዓለም አቀፉ ፕሪሚየም ስማርት ስልክ ብራንድ TECNO ዛሬ ከሆሊሁዱ […]

ኢትዮጵያ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ ብትሆንም ወደፊት ብሩህ ተስፋ እንደሚጠብቃት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2013 ኢትዮጵያ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ ብትሆንም ወደፊት ብሩህ ተስፋ እንደሚጠብቃት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡ ተማሪዎቹ ይህን ያሉት የከፍተኛ ትምህርት እና ሳይንስ ሚኒቴር፣ ከፒፕል ቱ ፒፕል፣ ከአፍሪኮም ሲምፖዚየምና ከኢንተርናሽናል ኔትወርክ ፎር ሀየር ኢጁኬሽን ኢን አፍሪካ ጋር ባዘጋጀው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውይይትና ክርክር መድረክ ላይ ነው፡፡ ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው ታላቁ የህዳሴው ግድብና […]

ኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያ ሳምንት ፌስቲቫልን እንዲጎበኙ ጥሪ ቀረበ።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2013 ኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያ ሳምንት ፌስቲቫልን እንዲጎበኙ ጥሪ ቀረበ።የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሣው፣ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እና የሴቶች፣ ወጣቶች እና ሕፃናት ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፌዎች በተገኙበት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ሳምንት በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2013 የኢትዮጵያ ሳምንት በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው። በ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት በ 3 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተዘጋጀው ፌስቲቲቫሉ ሀገሪቱ ያላትን ሀብትና የተፈጥሮ ፀጋ ለማስተዋወቅ እንዲሁም ወደ ኢንቨስትመንት አማራጭ ለመለወጥ ያለመ ነው። በፌስቲቫሉ ላይ የተለያዩ ክልሎች ልዩ መገለጫችን ያሉትን ባህላቸውን እያስተዋወቁበት ይገኛሉ። መሰል ፌስቲቫሎች ከሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር መዘጋጀታቸው […]

የዐረብ ሊግ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረም ለመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄ አቀረበ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2013  የዐረብ ሊግ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረም ለመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄ አቀረበ፡፡በጋዛ የተቀሰቀሰው ግጭት እንዲቆም እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ድርድሩ ሂደት ዳግም እንዲጀመር ነው ሊጉ ጥሪ ያቀረበው፡፡ የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በፈረንጆቹ ግንቦት 20 በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ዙሪያ ለመምከር ቀጠሮ መያዙን በድርጅቱ የአረብ ሊግ ተወካይ መጅድ አብደልፈታህ ተናግረዋል፡፡ ተወካዩ አህራም […]

በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮሮናቫይረስ ሞት ተመዘገበ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2013 በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮሮናቫይረስ ሞት ተመዘገበ በህንድ እየተባባሰ የመጣውን የኮሮናባይረስ ወረርሽኝ መቆጣጠር ያቃታቸው ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በህዝባቸው ዘንድ የነበራቸውን አመኔታ ዝቅ እንዲል አድርጎባቸዋል፡፡ በ24 ሰዓታት ውስጥ 4 ሽህ 529 ዜጎቿን በቫይረሱ የተነጠቀቸው ህንድ አሁንም በወረርሽኙ ጠንካራ ክንድ እየተደቆሰች ትገኛለች፡፡በየቀኑ በአማካይ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎች […]

የቴክኖው CAMON 17 ሰልፊ ላይ ባውጠነጠነ አስገራሚ ዘጋቢ ፊልም በመታገዝ ወደገበያ ገብቱዋል::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 የቴክኖው CAMON 17 ሰልፊ ላይ ባውጠነጠነ አስገራሚ ዘጋቢ ፊልም በመታገዝ ወደገበያ ገብቱዋል::ይህ ፈጠራ የታከለበት በፊልም የታገዘው የቴክኖ የማስመረቂያ ፕሮግራም ድርጅቱ ምርቱን ከማስተዋወቅ ባለፈ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና በሰብዓዊነት ላይ የበለጠ ጥረት ለማድረግ ያለውን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው:: ይህ ደግሞ ድርጅቱ በአለማችን ላይ በዘርፉ ቁንጮ እየሆነ መምጣቱን ይጠቁማል:: በአዲሱ ትውልድ በአለም አቀፍ ደረጃ […]

በአዲስ አበባ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች በታየባቸው ክፍተት የስራ ውል እንዲያቋርጡ ተደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 በአዲስ አበባ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች በታየባቸው ክፍተት የስራ ውል እንዲያቋርጡ ተደረገ:: ከ 60 እስከ 70 የሚጠጉ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ባሳዩት ክፍተት ውላቸው ተቋርጦ በሌሎች የመተካት ስራ እየሰራ እንደሆነ የ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖረት ቢሮ ምክትል […]

ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት ተከትበዋል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት ተከትበዋል ተባለ:: የጤና ሚኒስቴር በየ24 ሰዓቱ በሚያወጣው የኮቪድ 19 ወቅታዊ መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት መከተባቸውን ገልጿል፡፡ በተጨማሪም 2 መቶ22 ሺ 5 መቶ 60 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ […]

የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዞር የተደረገ ምክክር::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013  ጠ/ሚ ዐቢይ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዞር ከተቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ፈቃድ ለመስጠት እየተሰራ ባለው ስራ ዙሪያ ከአማካሪ ምክር ቤት አባላት ጋር መከሩ።ውይይቱ አዲስ የቴሌኮም ፈቃድ በመስጠት ሂደቱ ዙሪያ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዞር ከተቋቋመው […]