loading
በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013  በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮቪድ -19 ምክንያት የሞት መጠን አልተመዘገበም ተባለ፡፡ የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓትን ሪፖርት ባወጣዉ መረጃ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከረጅም ግዜ በኋላ በኮቪድ- 19 ምክንያት ሞት ያልተመዘገበበት ቀን ሆኗዋል፡፡ በ24 ሰዓቱ በተደረገ 4 ሺህ 974 የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በጽኑ የታመሙ 145 ሰዎች ሲሆኑ ከበሽታዉ ያገገሙ […]

የአገዛዝ እንጂ የፖሊሲ ለዉጥ አንፈልግም -ሱዳናዊያን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013  በሱዳን የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመፅ መንግስት ይቀየር ወደሚል አጀንዳ መሸጋገሩ ተሰማ፡፡ ሱዳን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ምክረ ሀሳብን ተቀብላ ተግባራዊ ያደረገችው የኢኮኖሚ መሻሻያ የፈጠረው የዋጋ ንረት ነው በሀገሪቱ ህዝባዊ አመፅ የቀሰቀሰው ተብሏል በተለያዩ የሱዳን ከተሞች በርካታ ሰዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስልጣኑን ይልቀቅ የሚል መፈክር ይዘው ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል ነው የተባለው፡፡ አጃንስ […]

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013 በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም:: በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮቪድ -19 ምክንያት የሞት መጠን አልተመዘገበም ተባለ፡፡ የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓትን ሪፖርት ባወጣዉ መረጃ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከረጅም ግዜ በኋላ በኮቪድ- 19 ምክንያት ሞት ያልተመዘገበበት ቀን ሆኗዋል፡፡ በ24 ሰዓቱ በተደረገ 4 ሺህ 974 የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች […]

እስካሁን የምርጫ ውጤት ተጠቃልሎ አልደረሰኝም-ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013  በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን የሁሉንም ምርጫ ክልሎች ውጤት ይፋ ማድረግ አለመቻሉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ። እስካሁን ባለው ሂደት ምርጫ ከተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች የ26ቱ ውጤት አለመድረሱን ቦርዱ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ፤ በድምር መዘግየት፣ በትራንስፖርት ችግር እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ምክንያት የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ማዕከል ተጠቃሎ አልደረሰም ብለዋል። […]

ህንድ በ39 ቀናት 100 ሺህ ዜጎቿን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ አጣች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013  በህንድ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ400 ሺህ በላይ ሲያሻቅብ ከዚህም ግማሽ ያህሉ ሞት በሁለተኛው ዙር ወረርሽኝ የተከሰተ ነው ተባለ፡፡ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተመታችው ህንድ እስካሁን ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ይፋ አድርጋለች፡፡ በህንድ 400 ሺህ 312 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ህይዎታቸውን ሲያጡ ከነዚህ መካከል 100 ሺህ የሚሆኑት የሞቱት በ39 ቀናት […]

ምርጫው ከነችግሮቹም ቢሆን የተሻለ ሂደት ታይቶበታል-ኢሰመጉ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013  6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ መሠረት የጣለና በአንፃራዊነት ስኬታማ እንደነበረ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ። ኢሰመጉ በቅድመ ምርጫ፣ በድምፅ መስጫ ዕለትና ድህረ ምርጫ ወቅቶች ያለውን አጠቃላይ ሂደት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። ምርጫው በተከናወነባቸው በአብዛኞቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጎላ የጸጥታ ችግር አለማጋጠሙን የገለጸው ተቋሙ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለሚፈጠሩ ችግሮች ምላሽ የሰጠበትን […]

የቻይና መንግስት ህገ ወጥ አዘዋዋሪ ነው- አንቶኒ ብሊንከን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013 አሜሪካ ቻይናና ሩሲያን ጨምሮ ከ10 በላይ ሀገሮችን በህገ ወጥ ሰዎች ዝውውርና በግዳጅ የጉልበት ብዝበዛ ከሰሰች፡፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰጡት መግለጫ ከሩሲያና ቻይና በተጨማሪ ማይናማር እና ቱርክ በዚሁ ተግባር ይሳተፋሉ የሚል ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ ብሊንከን በተለይ ሺንጂያንግ ግዛት አካሂዶታል ያሉትን የጅምላ እስር እና ተያያዥ ተግባራትን በመጥቀሽ የቻይና መንግስት […]

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ነው::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ነው እያካሄደ የሚገኘው፡፡ ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡ በምክር ቤቱ ስብሰባ መክፈቻ ላይ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላበረከተው አስተዋፅኦ የምክር ቤቱ አባላት አድናቆታቸውን በጭብጨባ ገልፀዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መሰብሰቢያ […]

የሰኔ ወር ዋጋ ግሽበት 24 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ አሳየ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ ሁኔታ የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ካለው ጋር ሲነጻጸር በ24 ነጥብ 5 ከመቶ ጭማሬ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡ የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ28 ነጥብ 7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በዳቦና እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው […]

በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ብሔራዊ የደኅንነት ስጋት ለመመከት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አብን ገለፀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ብሔራዊ የደኅንነት ስጋት ለመመከት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አብን ገለፀ፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈጻሚ ተወያይቶ  የደረሰባቸውን አቋሞች በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ አብን በመግለጫው የመራጩ ድምፅ እንዲከበር ሰላማዊና ሕጋዊ ጥረት እንደሚያደርግና የሕዝቡን ሐቀኛ ውሳኔ ያለማወላወል እንደሚቀበል አሳውቋል፡፡ በምርጫው የመሳተፉን ውሳኔ ያደረገው በዋነኝነት ከድርጅታዊ ፋይዳዎች ይልቅ ለሀገራዊ ፖለቲካው መረጋጋትና ለዴሞክራሲያዊ ተሞክሮ ግንባታ ከሚኖረው ፋይዳ አንፃር እንደሆነም ገልጿል፡፡ የምርጫው ሂደት አጠቃላይ ድርጅታዊ ቁመናውን የሚፈትሽበት መልካም አጋጣሚ መሆኑን እንደሚገነዘብ ነው በመግለጫው ያመላከተው፡፡ በቀጣይም ከሂደቱ ያገኛቸውን ተሞክሮዎችና ትምህርቶች በማካተትና ሁለገብ የማሻሻያ እርምጃዎች በመውሰድ ለብሔራዊ ፖለቲካ የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ገልጿል፡፡ የውጭ ወራሪዎችና የውስጥ ቦርቧሪዎች ከተቻለ ኢትዮጵያን ለየዘውጉ አምበሎች በታትኖ ከዓለም ካርታ ለማጥፋት፤ ካልሆነ ደግሞ ውስጣዊ አንድነት የሌላት፣ ደካማና ፍላጎታቸውን ያለማንገራገር የምትቀበል አድርገው ለማሽመድመድ እየተረባረቡ ይገኛሉ ብሏል። በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የብሔራዊ የደኅንነት ስጋት ለመመከት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑንም አብን ገልጿል፡፡ ማዕከላዊ መንግሥትና በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ አካላት ሀገሪቱን ከተደቀነባት የህልውና አደጋ ለመታደግ በሚደረገው ርብርብ የራሳቸውን ሚና በግልጽ ከመወሰን አንስቶ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ የብሔራዊ ደኅንነት እርምጃ እንዲወስዱም አብን ጥሪ አቅርቧል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ሀገር ወዳድ ዜጎችና በተለይም ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ሀገሪቱ ስለገጠማት የብሔራዊ የደኅንነት አደጋ ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ኢትዮጵያን ለመታደግ በአንድነት እንዲሰለፉም ጠይቋል፡፡ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተመድበው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን የትግራይ ሕዝብ አስፈላጊውን ጥበቃና እክብካቤ እንዲያደርግ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡