32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የከተማችን ነዋሪዎች ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ላበረከቱት ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና እና ተያያዥ ስብሰባዎች ከጥር 30 እስከ የካቲት 4 /2011 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
ጉባኤው በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ መላው ህብረተሰብ ለዘመናት ያካበተውን እውነተኛ የእንግዳ ተቀባይነት ባህሉን ተጠቅሞ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳዮች በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በፍፁም ትዕግስት ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት ፤ ለአጀብ ስራ መንገድ ተዘግቶ ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆን ድረስ አሽከርካሪዎች ትዕግስት ተላብሰው በመጠበቅ ፤ ህዝቡ ከፖሊስና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ጉባኤው በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ላበረከተው ጉልህ አስተዋፅኦ እንዲሁም ቀን ከሌሊት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ኃላፊነታቸውን በትጋት ለተወጡ ለመላው የፀጥታ አካላት ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ህብረተሰቡ የከተማውን ፀጥታ አሰተማማኝ እንዲሆን እያደረገ ያለውን የዘወትር ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል፡፡