loading
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ ገለጸ፡፡

32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ 32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በዚህ ሳምንት በመዲናችን አዲስ አበባ ይካሄዳል፤ ይህ ጉባኤ በሠላም ተጀምሮ አንዲጠናቀቅ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን እና የፀጥታ ሃይሎችን ያሳተፈ ኮማንድ ፓስት ተቋቁሟል ብለዋል፡፡

የከተማዋ  ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ የከተማችን ነዋሪዎች እንደተለመደው ከፀጥታ አካላት ጐን በመቆም ድጋፉቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት ይሁን አጠራጣሪ ጉዳዩች ሲያጋጥሙት በስልክ ቁጥር 011-1-26-43-77 / 011-1-26-43-59 ፣ /011-8-27-41-51 ፣ /011-1-11-01-11 እና 991 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚችል ኮሚሽኑ ገልፆል ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *