loading
32 ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች እና አሽከርካሪ መኪና የማያቆምባቸዉ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

32 ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች እና አሽከርካሪ መኪና የማያቆምባቸዉ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡
-ከፓርላማ መብራት  በውጭ ጉዳይ ሚ/ር መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ ኦምሎፒያ ወሎ ሰፈር ጃፓን ኤምባሲ ፍሬንድ ሺፕ ቦሌ ቀለበት መንገድ ኤርፖርት
-ከፓርላማ መብራት  በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  በብሄራዊ ቤተ መንግስት በፍልውሃ  ብሄራዊ ቲያትር  ሜክስኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ ፡፡
-ከፓርላማ መብራት  በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን  ፍልውሃና አምባሳደር ቲያትር ዙሪያውን
ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ዋናው በር ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከነገ ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
-ከጦር ሃይሎች – በሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች ፡፡
በኮካኮላ ድልድይ – በአብነት ተ/ኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ ሳር ቤት በቴሌ አድርገው ቀለበት መንገድ በሳር ቤት ወደ ቄራ ጎተራ፤ የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች  በአትላስ ዘሪሁን ህንፃ ሲግናል  ቀለበት መንገድ- ቦሌ ሚካኤል ሃኪም ማሞ ወደ ጎተራ
ቀለበት መንገድ -መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እንግሊዝ ኤምባሲ ቀለበት መንገድ መገናኛ አደዋ ጎዳና አዋሬ አራት ኪሎ፤ ከፊላሚንጎ ደንበል ጀርባ ወደ መስቀል ፍላወር መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቆ እንግዶች በአጀብ በሚያልፉበት ወቅት አሽከርካሪዎች ሆኑ እግረኞች ለፖሊስ አባለት አስፈላጊውን ትብበር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *