loading
የትራፊክ አደጋ አሁንም በቂ ትኩረት አልተሰጠውም ተባለ

አርትስ 01/13/2010
ይህ የተባለው አንድነት ለህይወት የተሰኘ የበጎ አድራጎት ማህበር ምስረታው ይፋ በሆነበት ወቅት ነው፡፡
ማህበሩ የትራፊክ አደጋ ቅነሳ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ለመስራት የተቋቋመ ሲሆን የትራፊክ አደጋ ቅድመ መከላከል ግንዛቤዎች፣ በአደጋ ለተጎዱ ሰዎች ፈጣን የመጀመሪያ ህክምና እና የአምቡላንስ አገልግሎት እንዲሁም የተጎጂ ቤተሰቦችን መደገፍ አብይ አላማው እንደሆነ የማህበሩ መስራች አቶ እንደለማው ግዛው ተናግረዋል፡፡
አዲስ አመትን ከመቀበል ጋር ተያይዞ በርካታ እንቅስቃሴዎች እተደረጉ ቢሆንም የትራፊክ አደጋ ቅነሳን ግን ከግምት ውስጥ ያስገቡ ስራዎች እንደሌሉ እና ጉዳዩ አሁንም በቂ ትኩረት እንዳልተሰጠው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኢኒስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ገልፀዋል፡፡
በ2010 ዓ.ም ብቻ 28 ሺ 361 የትራፊክ አደጋ ተመዝግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *