ግብፅ 75 ግለሰቦችን በሞት ቀጣች
አርትስ 05/13/2010
ግብጽ በሞት ከቀጣቻቸው ግለሰቦች መካከል በፈረንጆቹ 2013 የተፈጠረውን አመጽ ያስተባብሩ ነበር የተባሉት የተቃዋሚ መሪዎች ኢሳም አል ኢሪያን እና ሞሀመድ ቤልታጊ ይገኙበታል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው በዚሁ አመጽ እጃቸው ነበረበት የተባሉ ሌሎች 600 ሰዎች ከአምስት ዓመት ጀምሮ እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ የእስር ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡
የግብፅ መንግስት እንደሚለው ከሆነ ያኔ በተቀሰቀሰው አመጽ ከተሳተፉት የሚበዙት መሳሪያ የታጠቁ ሲሆን 8 የጸጥታ ሰራተኞችን ገድለዋል፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ከ800 በላይ በአመጹ የተሳተፉ ግለሰቦች በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የተገደሉ ሲሆን አሁን የተወሰነውን የጅምላ ፍርድም አውግዞታል፡፡