loading
አልበሽር ካቢኔያቸውን በትነው በአዲስ መልክ ሊያዋቅሩ ነው

አርትስ 05/13/2010
ሀገሪቱ የገጠማትን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመታደግ በሚል ምክንያት ነው ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አል በሽር 31 አባላት የነበረውን ካቢኔያቸውን በትነው ቁጥሩን ወደ 21 ዝቅ አድርገው ለማዋቀር የተገደዱት፡፡
ዘ ኢንዲያን ኤክፕረስ እንደዘገበው አሁን ላይ ሱዳን ከፍተኛ የነዳጅ፣ የምግብ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲሁም የዋጋ ግሽበት አጋጥሟታል፡፡
ሱዳን ለ20 ዓመታት ተጥሎባት የነበረው ማዕቀብ ከተነሳላት በኋላ ኢኮኖሚያዊ መሻሻል ታሳያለች ተብሎ ቢጠበቅም በገጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ ከውጭ መሰረታዊ ሸቀጦችን ለማስገባት ተቸግራለች፡፡
ከፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት የተሰጠው መግለጫ እንደሚያመላክተው አሁን ሀገሪቱ የወሰደችው ርምጃ የመንግስትን ወጭ በመቀነስ የተከሰተውን ቀውስ ለማተካከል ሁነኛ መፍትሄ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *