loading
ኢትዮጵያ የእንፋሎት ሃብቷን በሚገባ እየተጠቀመችበት አይደለም ተባለ

አርትስ 04/01/2011
የዉሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ፍሬህወት ወ/ማሪያም እንደገለፁት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የእንፋሎት ሃብት ቢኖራትም በዘርፉ ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የተሻለ ተጠቃሚ አልሆነችም፡፡
ሚኒስትር ዲኤታዉ ሃገሪቱ ያላትን እምቅ የእንፋሎት ሃብት መጠቀም ያስችላት ዘንድም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከተለያዩ ሃገራት ከተዉጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር የልምድ ልዉዉጥ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
የእንፋሎት ሃይል ከሌሎች የታዳሽ ሃይል ተመራጭ የሚያደርገዉ ዝቅተኛ የካርበን ልቀት ያለዉ በመሆኑና ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ላይ መዋል በመቻሉ እንደሆነ ዶ/ር ፍሬህወት ወ/ማሪያም ለአርትስ ቲቪ ገልፅዋል፡፡
ኬኒያ በአፍሪካ የእንፋሎት ሃብታቸዉን በአግባቡ ከተጠቀሙ ሃገራት ግምባር ቀደም ናት ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *