በአስመራና በትግራይ ከተሞች መካከል ንግዱ ተጧጡፏል
አርትስ 4/1/2011
የኤርትራ ፕሬስ እንደዘገበው የዛላምበሳ አስመራ መንገድ መከፈቱን ተከትሎ የንግድ ሸቀጦችን የጫኑ መኪኖች ወደ ሁለቱም ሀገሮች እንደልብ ምልልስ ጀምረዋል፡፡
ወደ ኢትዮጵያና ኤርትራ ለሚደረጉ ጉዞዎች የኬላ ፍተሻም ሆነ ቪዛ ስለማይጠየቅ በአስመራና በትግራይ ከተሞች የንግድ ልውውጥ ጨምሯል ነው የተባለው፡፡
በተለይ ከአስመራ ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ የተለያዩ ሸቀጦችን የሚሸምቱት ኤርትራዊያን ቁጥር ተበራክቷል፡፡
እስካሁን ባለው የትራንስፖርት ታሪፍ ከአዲግራት አስመራ የአንድ ሰው መጓጓዣ 200 የኢትዮጵያ ብር ወይም 110 የኤርትራ ናቅፋ መሆኑም ተገልጿል፡፡