loading
ቤምባ ሌላ የፍርድ ውሳኔ ሊተላለፍባቸው ነው

አርትስ 07/01/2011
የቀድሞው የደሞክራቲክ ኮንጎ ምትል ፕሬዝዳንት ጂያን ፒየር ቤምባ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይ ሲሲ) ከአሁን ቀደም በጦር ወንጀለኝነት 18 ዓመት ተፈርዶባቸው ነበር፡፡
አሁን ደግሞ በፍርድ ሂደቱ ምስክሮችን በጉቦ አባብለዋል ተብለው በተከሰሱበትና በሁለት ዓት ገደብ ነጻ ተብለውበት በነበረው ክስ የአምስት ዓም እስራት ይጠብቃቸዋል ነው የተባለው፡፡
ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው አቃቤ ህግ ቀድሞወንም ቢሆን ቤምባ ከፈጸሙት ወንጀል አንጻር ሁለት ዓመት ትንሽ ነው በአምስት ዓመት እስራት መቀጣት አለባቸው ብሏል፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንቱን ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይ ሲሲ) ከእስር በተጨማሪ 350 ሺህ ዶላር የገንዘብ እቅጣት ወስኖባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *