loading
የባንኮች አጠቃላይ ሀብት አንድ ትሪሊዮን ብር ደረሰ::

የግል ባንኮች ብድር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰጠው መብለጡም ተሰምቷል፡፡
ሪፖርተር እንደዘገበዉ የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዥና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ ጉዳዮች አማካሪና የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባል አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ እንደገለጹት፣ አሥራ ስምንቱ የአገሪቱ የግልና የመንግሥት ባንኮች በ2010 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ያስመዘገቡት የሀብት መጠን አንድ ትሪሊዮን ብር ሊደርስ የቻለው በ2002 ዓ.ም. ከነበረበት 167 ቢሊዮን ብር ተነስቶ ነው፡፡
አቶ ተክለ ወልድ ይህንን የገለጹት፣ ለእሳቸውና ለቀድሞው የባንኩ ምክትል ገዥና ዋና የኢኮኖሚ ባለሙያ ዶክተር ዮሐንስ አያሌው ላበረከቱት አገልግሎት በተዘጋጀው የሽኝትና የዕውቅና ፕሮግራም ላይ ነው፡፡ የፋይናንስ ዘርፉ ሁለንተናዊ ዕድገትን በማስመዝገብ ውጤታማ እንደነበር የገለጹት አቶ ተክለ ወልድ፣ የባንኮቹ የሀብት መጠንና ሌሎች ስኬቶች እያደጉ የመጡትና የተጠቀሰው የሀብት ዕድገት ውጤት የተገኘው ከ2002 ዓ.ም. በኋላ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ብሔራዊ ባንክ በተገበራቸው ፖሊሲዎች አማካኝነት ነው ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *