ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሃዋሳ ስቴዲየም ደማቅ አቀባበልና ምርቃት ላደረጉላቸው የሲዳማ ሽማግሌዎች እና ለሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ታላቅ ምስጋና አቀረቡ።
አርትስ 25/01/2011
ዛሬ በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝብ ፊት በሃዋሳ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎችን ምርቃት በክብር ተቀብለዋል። ስቴዲየሙም በሲዳማ ቄጤላ ደምቆ ውሏል።
ጠ/ሚኒስትሩ በንግግራቸው የኢህአዴግ ጉባኤ መክሮ አቅጣጫ ከሰጠባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹን ለታዳሚዎች አቅርበዋል ።
ስለ ድርጅቱ ኢህአዴግ ከመቼውም በላይ አንድንቱን አረጋግጦ መውጣቱን ፣ ምርጫን በተመለከተ ቀጣዩ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የዲሞክራሲ ተቋማት ሪፎርም በፍጥነት ተግባራዊ እንደሚደረግ፣ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩርት እንደሚሰጠው፣ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናነቷን ለማጠናከርና ለቱሪዝም ልማት ለአፍሪካዊያን የአፍሪካዊያን የቪዛ ሪፎርም ከቀጣዩንወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን፣ከኢኮኖሚ ልማት በግብርና (መስኖ ተኮር) እንዲሁም በኢንዱስትሪ (ኤክስፖርት ተኮር) ኢንቨስትመንት እንደሚጠናከር ተናግረዋል።
በተለያየ ስም የሚጠራው ወጣት ቄሮ፣ፋኖ ፣ዘርማ ብቻ ሳይሆን መላው የአገሪቱ ወጣት ለሰላምና ለልማት ግንባር ቀደም እንዲሆን ጠይቀዋል። በኢትዮጵያዊነቱ ሁሉም ተባብሮ እርስ በርሱ እንዲረዳዳ አሳስበዋል።