loading
የተባበሩት አረብ ኢመሬትስ መሃል አዲስ አበባ ውስጥ አነስተኛ ከተማ ልትገነባ ነው

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ትዕዛዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለገሃር ባቡር
ጣቢያ አካባቢ ፣ ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ባለሀብቶች የሚሰጥ 36 ሔክታር መሬት ማዘጋጀቱ
ተስምቷል፡፡
የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አልጋ ወራሽ ሼክ መሐመድን ቢን ዛይድ የሚመራ የልዑካን ቡድን፣
በቅርቡ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ ሲመጣ ይካሄዳሉ ከተባሉ ኩነቶች መካከል የ36 ሔክታር መሬት ርክክብ
ጉዳይ አንዱ ሲሆን፣ በንጉሣዊ ቤተሰቦች የተቋቋሙ ግዙፍ ኩባንያዎች በሚረከቡት ቦታ ላይ አነስተኛ
ከተማ ይገነባሉ ተብሏል፡፡

ይህ 36 ሔክታር መሬት የሚያካልለው ዕድሜ ጠገቡ የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ይዞታ የሆነውን
ለገሃር ባቡር ጣቢያ፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን (የአሁኑ ገቢዎች ሚኒስቴር)
መጋዘኖችና 1,500 ነዋሪዎች የሚኖሩባቸው ቤቶች ያረፉበት ነው፡፡
እንደ ሪፖርተር ዘገባ በቦታው ላይ ይገነባል የተባለው አነስተኛ ከተማ አፓርትመንቶች፣ ሆቴሎች፣ የገበያ
ማዕከላት፣ የመዝናኛ ማዕከላት፣ አረንጓዴ ቦታዎችና የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን የሚያካትት ሲሆን
ለኩባንያዎቹ ተላልፈው በሚሰጡት ቦታዎች ላይ የሚገኙ 1,500 ነዋሪዎች፣ ከዚህ ቀደም
እንደተለመደው የሚፈናቀሉ ሳይሆኑ በፕሮጀክቶቹ ይታቀፋሉ ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *