loading
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ለውጡ ስኬታማ መሆን ካልቻለ የመጨንገፍ ዕድል ይገጥመዋል” አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬ የምክር ቤት ውሏቸው በሃገሪቱ እየመጣ ያለው ለውጥ ስኬታማ መሆን ካልቻለ የመጨንገፍ እድል ይገጥመዋል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህግ የበላይነት፣ በጸጥታ እና መፈናቀል ጉዳዮች ላይ ባተኮረው በዚሁ ማብራሪያቸው እንደተናገሩት ለውጡን ለማጨናገፍ እየሰሩ ያሉ አካላትን ማስቆም ያስፈልጋል ብለዋል።

በመሆኑም መንግስት ይህን ድርጊት በበላይነት የሚመሩትን አካላት ለይቷል ነው ያሉት። መንግስት እነዚህን አካላት ከድርጊታቸው የሚያስቆም አካሄድ በመከተል ላይ መሆኑንም ተናግረዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰቱ መፈናቀሎች እና ጥቃቶች ለፖለቲካ አላማ ተብለው የተቀነባበሩ ሴራዎች መሆናቸውን ገልጸው ጉዳዩን በጥንቃቄ ይዘን እየሰራንበት ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የመፈናቀልና ዘረፋ ሁኔታ መፈጸሙንና ይህም በኢትዮጵያ ታሪክ የሚወሳ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተሰራ የተባለው ወንጀል ግን ወደ ዘር ማጥፋት መሄድ የለበትም ነው ያሉት ። በችግሩ ያልተጠቃ ወገን ስለሌለ ዝርዝር ጥናት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

“የደቦ ፍርድ በፍጹም ሊቀጥል አይገባም፡፡ መንግስትም ቢሆን የግጭት ሁኔታዎችን ለይቶ በማምከን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ጥረት አድርጓል ፣ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *