loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በጀርመንና ፈረንሳይ የፋዊ የስራ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበላቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያደርጉት በሀገራቱ መሪዎች በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት መሆኑ ታውቋል፡፡ እንደውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪው ሳምንት ጉብኝታቸውን ይጀምራሉ፡፡

ቀዳሚ ጉብኝታቸውን በፈረንሳይ የሚጀምሩ ሲሆን፥ በቆይታቸውም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ይወያያሉ ተብሏል።

በመቀጠልም ወደ ጀርመን አቅንተው፥ በዚያም ከመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ላይ ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ከሚውጣጡ 25 ሺህ ኢትዮጵያውያን ጋር በፍራንክፈርት ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *