loading
በክሪሚያ አንድ ኮሌጅ ላይ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ የ18 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ

ሩሲያ ከዩክሬን በቅርቡ ወደ ግዛቷ በቀላቀለቻት ክሪሚያ በአንድ ኮሌጅ ላይ በፈነዳ
ቦንብ በትንሹ የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ12 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለፀ።

ፍንዳታውን ተከትሎ የፀጥታ አካላት ትምህርት ቤቱን መክበባቸው እየተነገረ ነዉ።

የአካባቢው ባለስልጣናት ምንነቱ ያልታወቀው ተቀጣጣይ መሳሪያ ከርች በሚገኝ የቴክኖሎጂ ኮሌጅ ውስጥ መፈንዳቱን አስታውቀዋል።

በዘሬዉ እለት እየወጡ ያሉ መረጃዎች ፍንዳታው በጋዝ ፍንዳታ መከሰቱን የሚገልፁ ቢሆንም፥ የሩሲያ ብሄራዊ ዘብ ባለስልጣናት ግን የሽብር ጥቃት አይነት ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከብረት የተዘጋጀው ተቀጣጣይ መሳሪያ በተማሪዎች የመመገቢያ ስፍራ ላይ ድንገተኛ ጉዳት ማስከተሉን በምርመራዉ የተሳተፉ አካላት ይፋ አድርገዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *