loading
ግዙፉ የጣልያን ኩባንያ በአፍሪካ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን በኢትዮጵያ ከፈተ

አርትስ 12/02/2011
ካልዜዶኒያ የተባለው ግዙፍ የጣልያን የአልባሳት ፋብሪካ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ፋብሪካውን  የመቐለ ከተማ አስመረቀ።

ፋብሪካው ለምፅዋ ወደብ ባለው ቅርበት ለምስራቅ አፍሪካ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ጉልህ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት የተገለጸ ሲሆን ለአንድ ሺ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩ ባለፈ ለውጭአገራት ከሚያቀርበው ምርቱ እንደ መነሻ በየወሩ 22 ሚሊዮን ብር ገቢ ማስገኘት መጀመሩ ታውቋል  ሲል የውጨ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም የፋብሪካውን መመረቅ አስመልክተው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *