loading
በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያን ቡና የማስተዋወቅ ስነ-ስርዓት ተካሄደ

አርትስ 13/02/2011
በደቡብ ኮሪያ ሴኡል የሚገኘው የኢትዮጵያኤምባሲ ለሁለት ቀናት በደቡብ ኮሪያበተካሄደው የቡና ማስተዋወቂያ ፌስቲቫል(Youth Coffee Festival) ላይ የሀገራችንንቡና አስተዋውቋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የዓለማችንን ልዩ ልዩተመራጭ የቡና ጣዕሞች እና ዝርያዎችንየማስተዋወቅ ስራ አከናውኗል፡፡

ኤምባሲው የኢትዮጵያን ባህላዊ የቡናአፈላል ስርዓት ለታዳሚዎች አሳይቷል፡፡

ታዳሚዎችም ከኢትጵያ ቡና አምራቾችናነጋዴዎች ጋር የገበያ ትስስር መፍጠርእንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

በተያየዘም የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች  በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው በደቡብ ኮሪያ ሴኡል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከግዮንዥ ግዛት አነስተኛና መካከለኛ ኩባንያዎች ማህበር  ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ላይ ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ ከማህበሩ የተውጣጡ የኮንስትራክሽን ፣የምግብ ማቀነባበሪያ ፣የውበትና ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች  ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሁኔታ  ለኢንቨስትመንት አመቺ በመሆኑ ኮሪያውያን ኩባንያዎች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ  ተደርጎላቸዋል፡፡

በኤምባሲው የቢዝነስ ዲፕሎማሲሚኒስትር አማካሪ አቶ አምኃ ኃይለጊዮርጊስበኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንትአማራጮች እንዲሁም ማበረታቻዎችንበተመለከተ ለኩባንያዎቹ ማብራሪያሰጥተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *