loading
በቻይና በአንድ መዋለ ህጻናት ትምህርት ቤት በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 14 ህፃናት ተጎድተዋል ተባለ

በቻይና በአንድ መዋለ ህጻናት ትምህርት ቤት በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 14 ህፃናት ተጎድተዋል ተባለ

አርትስ 16/02/2011

የሃገሪቱ ፖሊስ እንዳለው እድሜዋ 39 የሆነች እናት የኩሽና ቢላ ይዛ ወደ ትምህርተ ቤቱ በመግባት ህፃናቱ በጫዋታ ላይ እያሉ በያዘቸው ቢላ እነዚህን ህጻናት አቁሰላለች፡፡

ሴትየዋ ጠቃቱን ያደረሰችበት ምክኒያት እስካሁን በፖሊስ ግልፅ ባይደርግም በማህበራዊ ድህረ ገፆች እየተወራ እንዳለው ከሆነ  ግን መንግስትን ዕየተቃወመች ነበር ብለዋል፡፡

በቅፅል ስሟ ሊዉ የተባለችው ይህች ሴት ከቦታው ብዙም ሳትርቅ በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ ሁለት ህፃናት ሙተዋል ተብሎ እየተወራ ያለውን ፖሊስ ውሸት ነው ቢለውም የአካባቢው ሰዎች ግን ጉዳቱ ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል እያወሩ ነው፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበዉ  እንደ ፖሊስ ጥርጣሬ ከሆነ ይህን አይነት ደርጊት የሚፈጽሙት በግላቸው ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ፀብ ካላቸው አሊያም የአዕምሮ ህሙማን ከሆኑ ነው ብሏል፡፡ ተጨባጭ መረጀዎች ቀጣይ ሊወጡ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *